Get Mystery Box with random crypto!

#የስጦታ_ዋጋ ባል ሚስቱን የስጦታ መሸጫ መደብር ይዟት ይሄዳል። 'የኔ ማር እስኪ ለእናቴ ስጦታ | ምርጥ መጣጥፎች

#የስጦታ_ዋጋ

ባል ሚስቱን የስጦታ መሸጫ መደብር ይዟት ይሄዳል። "የኔ ማር እስኪ ለእናቴ ስጦታ የምሰጣት ቆንጆ ስጦታ ምረጪልኝ አላት።

እርሷም በውስጧ ስለቀናች በጣም ርካሽ ስጦታ መረጠች። ስጦታውን አስጠቀለለና ባል ወደ እናቱ ጋር እንደሚሄድ ነግሯት ተለያዩ።

ማታ ላይ የመረጠችውን ስጦታ ይዞ መጣና ሰጣት። "ስጦታው ለአንቺ ነው። ሰርፕራይዝ ላደርግሽ ፈለኩ ግን ምርጫሽን ስላላወኩ ራስሽ እንድትመርጪ አደረኩኝ።"አላት። ሚስት በስራዋ አዘነች።

ሌላውን እንደ ራሷ ብትወድ ኖሮ ስጦታዋ ያማረ ይሆን እንደነበር ተረዳች። መልካምነት ለራስ ነዉ የሚባለው ለዚህ ነው።
#ምርጥ_መጣጥፎች