Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ መጣጥፎች

Telegram kanalining logotibi mirtmetatifochinaababaloch — ምርጥ መጣጥፎች
Telegram kanalining logotibi mirtmetatifochinaababaloch — ምርጥ መጣጥፎች
Toifalar: Kattalashtirilmagan
Til: Oʻzbek tili
Obunachilar: 1.09K
Kanalning ta’rifi

ለሰዉ ልጅ ጠቃምና አስተማሪ የሆኑ መጻሕፍት እና ድህረገጾችን ማድረስ ጥቅሙ የጋራ ነዉ።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


Oxirgi xabar

2023-05-09 00:00:14 #ስሜቶችህ_አሻንጉሊት_የሆንክ_ያህል_ይጫወቱብሀል

“ሃሳቦችህን እንዲህ ሰድራቸው - አንተ ሽማግሌ ነህ፤ ከዚህም በኋላ ጥቂት እድሜ ብቻ ነው ያለህ - በእነዚህ ነገሮች ከዚህ በኋላ አትገዛም፤ እያንዳንዱ ስሜቶችህ እንደ አሻንጉሊት አይጎትቱህም፤ አሁን ላይ ስላለህ ሕይወት አታማርርም ወይም መጻኢ ቀናቶችህን በፍርሃት አትጠብቃቸውም”
#ማርከስ_አውሬሊየስ

ሰው መጥቶ እኛን ሊያዘን እና አለቃ ሊሆንብን ሲሞክር እንበሳጫለን። እንዴት እንደምለብስ አትነግረኝም፣ እንዴት እንደማስብ፣ ስራዬን እንዴት እንደምሰራ፣ እንዴት መኖር እንዳለብኝ… ይህም የሆነው እኛ ነጻ ሰው ነን ብለን ስለምናስብ ነው።

ለራሳችን እኛው ራሳችን በቂ ነን።

ይህንንም ነው ለራሳችን ስንነግረው የኖርነው።
ሆኖም የማንስማማበትን ሃሳብ የሆነ ሰው ካቀረበልን፣ ውስጣችን እንድንሞግተው ይነግረናል። የሆነ ሰው የማንወደውን ነገር ካደረገብን እንበሳጫለን። መጥፎ ሁነት ሲገጥመን እናዝናለን፤ ድባቴ ውስጥ እንገባለን ወይም እንጨነቃለን። ሆኖም ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መልካም ነገር ከሆነልን በድንገት ደስተኛ፣ ተጫዋች እና ተጨማሪ ፈላጊዎች እንሆናለን።

ማንም ሰው ከስሜቶቻችን በላይ በእኛ ላይ አይጫወትም። ልክ አሻንጉሊት እንደሆንን ሁሉ ስሜቶቻችን ይጫወቱብናል፤ ይህን ማስተዋል ስንጀምር በስሜቶቻችን መመራት ማቆም እንዳለብን እንረዳለን።

ስሜቶቻችን ሳይሆኑ እኛ ነን አለቃ መሆን ያለብን፤ ምክንያቱም ለራሳችን እኛው ራሳችን በቂ እና ነጻ የሆንን ነንና።

#የለት_ፍልስፍና መጽሐፍ
#ምርጥ_መጣጥፎች
180 viewsምርጥ መጣጥፎች, 21:00
Ochish/sharhlash
2023-05-09 00:00:12
164 viewsምርጥ መጣጥፎች, 21:00
Ochish/sharhlash
2023-05-08 23:58:33 ስትሰጥ የተረፈህን አትስጥ ፣
የማትፈልገዉን አትስጥ ! እሱ
መስጠት አይባልም መጣል ነዉ ።
ለሰዉ ልጅ መስጠት ያለብህን ለአንተ አስፈላጊ የሆነና ዉድ የሆነዉን ነገር ነዉ!

የቆሸሸ ፣ የተቀደደ ፣ የተረፈህ ፣ ማትፈልገዉ ፣ የጠበበህ ለሰዉ ምትሰጥ እመነኝ በፍፁም ሰጠዉ ብለህ እንዳታስብ ! የምሰጥ ከሆነ ለሰዉ ልጅ ዉድ ነገርህን ስጠዉ !
ፈጣሪህ አንድም ሳይሰስት እጅግ ብዙ ዉድ ነገሮችን በነፃ እንደሰጠህ አስተዉስ !
በነፃ የተሰጠህን በነፃ ስጥ !

የምትሄድበት እንዳይጠፋህ
የመጣህበትን አትርሳ !
#ምርጥ_መጣጥፎች
169 viewsምርጥ መጣጥፎች, 20:58
Ochish/sharhlash
2023-05-08 23:58:31
164 viewsምርጥ መጣጥፎች, 20:58
Ochish/sharhlash
2023-05-04 18:37:05 #ጭንቀት

አንዳንድ ሰዎች በየምክንያቱ ይጨናነቃሉ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን አብዛኛዎቹ የምንጨነቅባቸው ነገሮች ቀድሞውኑ መሰረት የሌላቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌነት የሚከተለውን የአንድ ጥናት ውጤት እንመልከት፡፡ የምንጨነቅባቸው ነገሮች . . .

1. 40% በፍጹም ለማይደርስብን ነገር

2. 30% ምንም ልንለውጠው ስለማንችለው ስላለፈው ነገር

3. 12% ሰዎች ስለእኛ ስለሚናገሩብን ፍርድ፣ ወሬና ሃሜት

4. 10% ስለጤንነታችን (ስለተጨነቅን የሚብስ)

5. 8% ስለእውነተኛ ልናስብበት ስለሚገባ ሁኔታ

በፍጹም ለማይደርስብን ነገር ከተጨነቅን . . . ያለን አማራጭ ምክንያታዊነትን ማዳበር ነው፡፡ ሁኔታው ሊደርስብንና ላይደርስብን የሚችልበትን የእድል መጠን አመዛዝነን ያለመድረሱ ሁኔታ ካመዘነ፣ መጨናነቅን የማቆምን ሂደት መጀመርና እየተዉ መሄድ የግድ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን እንዲሁ ምክንያት ፈልገው የመጨነቅ “ሱስ” አለባቸው፡፡
ይህ ዝንባሌ የሚመጣው ለረጅም ጊዜ በአጣብቂኝ ሁኔታ ከማሳለፍና ስሜታችን የጭንቀት ሰለባ ሆኖ ከመክረሙም የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡ ያም ሆነ ይህ ፍጹም የማይደርስ ነገር ተለይቶ ሊታወቅና ከስሜታችን የደም ዝውውር ውስጥ ሊወገድ ይገባዋል፡፡

ምንም ልንለውጠው ስለማንችለው ስላለፈው ነገር ከተጨነቅን . . . ያለን አማራጭ ፈጽሞ አንዴ የሆነ ነገር መሆኑንና ምንም ብናደርግ ልንለውጠው እንደማንችል በመቀበል አእምሮን በአዳዲ ነገሮች መሙላት ነው፡፡ ይህን ማድረግ ካልፈለግን ግን እስቲ አንዴ የሆነውንና ያለፈውን ነገር ለመለወጥ የአንድ ወር ጊዜ እንስጠውና የምንችለውን ያህል እንሞክርና ካልቻልን ነገሩን ለመተው ለራሳችን እድል እንስጠው፡፡

ሰዎች ስለእኛ ስለሚናገሩብን ፍርድ፣ ወሬና ሃሜት ከተጨነቅን . . . ያለን አማራጭ መቆጣጠር የማንችለውን የሰውን ባህሪይ ለመቆጣጠር ከመጦዝ ይልቅ መቆጣጠር የምንችለውን የራሳችንን በሆነ ባልሆነው የመጨነቅ ዝንባሌ ለመቆጣጠር መስራቱ ይመረጣል፡፡ ሰዎች ስለአንተና በአንተ ላይ የሚሉት ነገር አንተ ካልፈቀድክለት በስተቀር ምንም ሊያደርግህም እንደማይችል አትዘንጋ፡፡ ብትችል ወሬው አንተ ጋር የማይደርስበትን መንገድ ፍጠር፡፡ ካልቻልክ ደግሞ ወሬው ወደ ስሜትህ የማይደርስበትን ጥንካሬ አዳብር፡፡

ስለጤንነታችን (ስለተጨነቅን የሚብስ) ከተጨነቅን . . . ያለን አማራጭ ስለጤነታችን የሚያሳስበን ሁኔታ ካለ ያንን ለማስቀረት ወይም ለመቀልበስ የምንችለውን ያህል መሞከር ነው፡፡ ጭንቀታችን ግን “ምናልባት እታመም ይሆን” የሚል ከሆነ፣ ይህ የራስ በራስ ትንበያ እንደሚፈጸም አትጠራጠር፡፡ ጭንቀት በሽታን የመሳብ ባህሪይ አለውና፡፡

ስለእውነተኛ ልናስብበት ስለሚገባ ሁኔታ ከተጨነቅን . . . ያለን አማራጭ በቅድሚያ፣ ሁኔታው በትክክልም የሚያሳስብና በቅጡ ካልያዝነውም የሚስጨንቅ ጉዳይ ስለሆነ ማሰባችንና በመጠኑም ቢሆን መጨነቃችን ትክክለኛው መሆኑን አምኖ መቀበል አስፈላጊ ነው፡፡ ሲቀጥል ያሳሰበንን ሁኔታ በምን መልኩ ብንጋፈጠው ልናሸንፈው እንደምንችል በሚገባ ማሰብን ይጠይቃል፡፡ አእምሮን በጭንቀት ከመሙላት ይልቅ ትክክለኛውን ምላሽ በማሰብ መሙላት በብዙ እጥፍ ይመረጣል፡፡ በጉዳዩም ላይ ሰውን ማማከሩም አንዱ መንገድ ነው፡፡
#ምርጥ_መጣጥፎች
297 viewsምርጥ መጣጥፎች, 15:37
Ochish/sharhlash
2023-05-04 18:36:42
214 viewsምርጥ መጣጥፎች, 15:36
Ochish/sharhlash
2023-05-03 22:51:30 #የስጦታ_ዋጋ

ባል ሚስቱን የስጦታ መሸጫ መደብር ይዟት ይሄዳል። "የኔ ማር እስኪ ለእናቴ ስጦታ የምሰጣት ቆንጆ ስጦታ ምረጪልኝ አላት።

እርሷም በውስጧ ስለቀናች በጣም ርካሽ ስጦታ መረጠች። ስጦታውን አስጠቀለለና ባል ወደ እናቱ ጋር እንደሚሄድ ነግሯት ተለያዩ።

ማታ ላይ የመረጠችውን ስጦታ ይዞ መጣና ሰጣት። "ስጦታው ለአንቺ ነው። ሰርፕራይዝ ላደርግሽ ፈለኩ ግን ምርጫሽን ስላላወኩ ራስሽ እንድትመርጪ አደረኩኝ።"አላት። ሚስት በስራዋ አዘነች።

ሌላውን እንደ ራሷ ብትወድ ኖሮ ስጦታዋ ያማረ ይሆን እንደነበር ተረዳች። መልካምነት ለራስ ነዉ የሚባለው ለዚህ ነው።
#ምርጥ_መጣጥፎች
235 viewsምርጥ መጣጥፎች, 19:51
Ochish/sharhlash
2023-05-03 22:51:00
207 viewsምርጥ መጣጥፎች, 19:51
Ochish/sharhlash
2023-05-03 22:40:25 #አልመህ_ተኩስ!

አንድ ንጉስ ከአጃቢዎቹ ጋር በአንድ ጫካ ውስጥ ሲዘዋወር አንድ ዛፍ ላይ ያየው ነገር ትኩረቱን ሳበው፡፡ በዚህ ትልቅ ዛፍ ላይ የተለያዩ ክብ ቅርጽ ያላቸው ኢላማዎች ተስለዋል፡፡ የገረመው ነገር፣ እያንዳንዳቸው ኢላማዎች መካከል ምንም ሳይስቱ ኢላማቸውን በትክክል የመቱ ቀስቶች ተሰክተው ይገኛሉ፡፡ ንጉሱ በጣም ተገረመና፣ “እነዚህን ኢላማዎች ሁሉ በትክክል አነጣጥሮ የመታውን ሰው ለሰራዊቴ አለቃነት እፈልገዋለሁና ፈልጋችሁ አግኙልኝ” አለ፡፡

ልክ ይህንን ተናግሮ እንደጨረሰ አንድ ወጣት ልጅ ብዙ ቀስቶችን ተሸክሞ እየገሰገሰ ንጉሱ ጋር ደረሰ፡፡ ንጉሱ፣ እነዚህን ሁሉ ኢላማዎች በትክክል የመታው ሰው እሱ መሆኑን ጠይቆ የአዎንታ መልስ ካገኘ በኋላ እንዴት እንደዚህ አነጣጣሪ ሊሆን እንደቻለ ጠየቀው፡፡ የልጁ መልስ አጭርና ግልጽ ነበር፣ “በመጀመሪያ ቀስቴን ወጥሬ በዛፉ ላይ እሰካዋለሁ፡፡ ከዚያም ወደ ዛፉ በመሄድ በተሰካው ቀስት ዙሪያ የክብ ምልክትን አስቀምጥበታለሁ” በማለት እንደዚያ አነጣጣሪ ያስመሰለውን እውነት ፍርጥ አደረገና ነገረው፡፡

ይህ መሰረታዊና ቀላል አፈ-ታሪክ የብዙ ሰዎችን የሕይወት ዘይቤ ያንጸባርቃል፡፡ ይህ ወጣት በመጀመሪያ ዓላማን አድርጎ አልነበረም ያንን ዓላማ ለመምታት ጥረት ያደረገው፡፡ በቅድሚያ ወዳሻው ቀስቱን ከለጠጠና ከሰነዘረ በኋላ ቀስቱ ያረፈበትን ስፍራ ነው እንደዓላማ በመቁጠርና ልክ ዓላማውን እንደመታ ለማስመሰል በዙሪያው ክብን ያበጀለት፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንዲሁ ናቸው፡፡

በመጀመሪያ ዒላማንና ግብን አቅደው በዚያ ባቀዱት መሰረት ሊተኩሲ ሲገባቸው ከተኩሱ በኋላ ቀስቱ ያረፈበትን ነው እንደግብ የሚቆጥሩት፡፡ በሌላ አባባል፣ ያገኘነውን፣ የመሰለንንና የቀለለንን ነገር ካደረግን በኋላ በዚያ ባደረግነው ተግባር ዙሪያ ዓላማን ለመፍጠር መሞከር የሞኝነት ሁሉ ሞኝነት ነው፡፡ ዓላማ ከሌለን የምንሄድበትን አናውቅም፡፡ ግብም ከሌለን ተኩሰን የመታነው ነገር ሁሉ እንደ ግብ ስለሚቆጠር ይህንና ያንን ስናደርግ ጊዜያችን ይባክናል፡፡ ለዚህ ነው በዓላማና በግብ የምንመራ ሰዎች መሆን ያለብን፡፡

አንድ በር ተከፍቶ ስላገኘህ ብቻ ከገባህ በኋላ የገባህበትን ዓላማ ለማግኘት አትሯሯጥ፤ በመጀመሪያ በዚያ በር የመግባትህ ጉዳይ ከሕይወትህ ዓላማ ጋር መስማማቱን አረጋግጥ፡፡

አንድ ሃገር የመሄድ እድል ስለተገኘ ብቻ ከሄድክ በኋላ ዓላማ ለመፍጠር አትሂድ፤ በመጀመሪያ ወደዚያ ሃገር የመሄድህ ጉዳይ ከሕይወትህ ዓላማህ ጋር አለመጣረሱን አረጋግጥ፡፡

አንድ ሰው ትኩረትና የመፈቀር ስሜት ስለሰጠህ ብቻ ሁለንታንህ በመስጠት ግንኙነት ውስጥ ከገባህ በኋላ ዓላማ ለመፍጠር አትታገል፤ ጓደኛንም ሆነ ፍቅረኛን ከዓላማህ አንጻር ምረጥ፡፡

ስራህንም እንደዚያው! ትምህርትህንም እንዲዚያው! የሕይወትህን ዋና ዋና ክፍሎችም እንደዚያ!

ከዓላማ ተነሳ እንጂ ተነስተህ ከተጓስክ በኋላ ዓላማህን ለማግኘት አትባክን፡፡ ዓልመህ ተኩስ እንጂ የተኮስከው ነገር የመታውን ነገር ሁሉ ዓላማህ እንደሆነ በማሰብ ራስህን በማታለል ዘመንህን አታባክን፡፡
#ምርጥ_መጣጥፎች
191 viewsምርጥ መጣጥፎች, 19:40
Ochish/sharhlash
2023-05-03 22:32:02
160 viewsምርጥ መጣጥፎች, 19:32
Ochish/sharhlash