"YeneTube" Telegram kanali

Telegram kanalining logotibi yenetube — YeneTube
1,311
Kanaldagi mavzular:
Artland
Shegerhive
Ethiopia
Addisababa
Hiking
Marakiconsultancy
Free
Telegram kanalining logotibi yenetube — YeneTube
Kanaldagi mavzular:
Artland
Shegerhive
Ethiopia
Addisababa
Hiking
Marakiconsultancy
Free

"YeneTube" Telegram kanali

Kanal manzili: @yenetube
Toifalar: Kattalashtirilmagan
Obunachilar: 165,242 (Yangilash sanasi: 2021-12-09)
Kanalning ta’rifi

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Sharhlar

Izohni e’lon qilish uchun tizimga kirish zarur.Oxirgi xabar 8

2021-12-01 09:38:05
Picture 1 from YeneTube 2021-12-01 09:38:05
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ!

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ምክትል ጠቅላይ ሚኒሰትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ደመቀ መኮንን አቀባበለ አድርገውላቸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
13.9K views
Ochish/sharhlash
2021-12-01 09:37:36
Picture 1 from YeneTube 2021-12-01 09:37:36
🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦
በአሜሪካ ና ካናዳ በስኮላርሺፕ የመማር ዕድል!

ያለ ቅድመ ክፍያ ለመመዝገብ ቴሌግራም ቦት ላይ አፕላይ ያድርጉ! 👇
@marakischolarshipbot


አድራሻ: ቦሌ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222

ለበለጠ መረጃ @marakiconsultant

ቴሌግራም ቻናል👇
@marakiconsultancy
13.4K views
Ochish/sharhlash
2021-12-01 09:37:36
Picture 1 from YeneTube 2021-12-01 09:37:36
የግርግዳ ላይ ውብና ማራኪ ምስሎችን ባለ 3 ,4, 5 piece wall art አቅርበንላችኋል ለቤትዎ፣ለቢሮዎ፣ለሆቴልዎ፣ለስጦታ፣ለካፌዎ
በፈለጉት መጠን ማሰራት ለምትፈልጉ ሰርተን ያሉበት ድረስ መተን ገጥመን እንሰቅልሎታለን።
#free delivery
👉0942382407
👉 0943302837
ለበለጠ መረጃ telegram channal ይቀላቀሉ
👉 join our channals @twincreatives
@Twinsart
Contact us on telegram users
👉 @suravell
@Kir455
13.9K views
Ochish/sharhlash
2021-11-30 23:58:52 ተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ተመቷል በሚል በድጋሜ የሚሰራጨው መረጃ የሐሰት መሆኑ ተገለጸ!

የተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ በመንግስት ተመቷል በሚል በሽብርተኛው የህወሓት ቡድንና በአቀንቃኞቹ የሚናፈሰው ወሬ ሐሰት መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።ከዚህ ቀደምም ግድቡ ተመቷል በሚል በጥፋት ቡድኑ ተመሳሳይ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ተሰራጭቶ እንደነበር ይታወሳል።

በመንግስት የተመታው የተከዜ ግድብ ሳይሆን ተከዜን ተሻግሮ ወረራ የፈፀመው የሽብር ቡድኑ ነው።ይሁንና የተከዜ ግድብ ባለፈው ክረምት ሙሉ በመሆኑ ውሃው እንዲፈስ በማድረግ የሀሰት ፕሮፓጋንዳውን እውነት ለማስመሰል ጥረት ሊያደርግ እንደሚጥር ይገመታል።የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ሙያተኛ ባልሆኑ ሰዎች፣ ከታለመለት ዓላማ ውጪ እንዲሰራ ከተደረገ ከፍተኛ መጠን ያለው ጉዳት ሊደርስበት እንደሚችል ይታመናል።

በመሆኑም የሽብር ቡድኑ ህዝብን ለማሸበርና ዓለም አቀፍ ትኩረት ለመሳብ ውሃውን ሊለቅ ስለሚችል በግድቡ የታችኛው ተፋሰስ አካባቢ በተለይም በጣንቋ አበርገሌ፣ በጠለምት፣ በቃፍታ ሁመራ፣ በጠገዴ፣ በአበርገሌና በወልቃይት አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተቋሙ አሳስበዋል።መረጃ የደረሳችሁ የህብረተሰብ ክፍሎች መልዕክቱን በማስተላለፍ ትብብር እንድታደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

የተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሙሉ በሙሉ በሽብርተኛ ቡድኑ ቁጥጥር ስር ከመዋሉ በፊት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ መለዋወጫ ተሟልቶለትና ከሁለት መቶ በርሜል በላይ የተርባይን ዘይት አቅርቦት ቀርቦለት በጥሩ ሁኔታ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነበር ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ገልጾአል።

(ኢ ፕ ድ)
@YeneTube @FikerAssefa
2.5K views
Ochish/sharhlash
2021-11-30 20:58:11 ትዊተር ኩባንያ "በቃ!" በሚል መሪ ቃል የምዕራቡ ዓለም ሀገራት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በማውገዝ የትዊተር ዘመቻ የሚያደርጉ የኢትዮጵያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የትዊተር ገጾችን እንደዘጋ ተሰምቷል። ኩባንያው ስንት የትዊተር ገጾችን እንደዘጋ ግን ገና አልታወቀም። የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤትም ትዊተር ኩባንያ አፍቃሬ-ኢትዮጵያ የሆኑ ድምጾችን እያፈነ ነው ብሎ እንደሚያምን ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የፕሬስ ሴክሬታሪ ቢልለኔ ሥዩም ተናግረዋል። የሕወሃት ደጋፊዎች በኩባንያ ውስጥ በብዛት እንደሚገኙ መንግሥት ለኩባንያው ማሳወቁንም ቢልለኔ አስታውቀዋል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
10.3K viewsedited  
Ochish/sharhlash
2021-11-30 20:21:03
Picture 1 from YeneTube 2021-11-30 20:21:03
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ለዶ/ር ኢሌኒ ዘውዴ ገብረ መድኅን ሰጥቶት የነበረውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንዲሰረዝ ወሰነ!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሰኔ 29/ 2005 ዓ.ም ለዶ/ር ኢሌኒ ገ/መድኅን የኢትዮጵያ ምርት ገበያን በማቋቋምና በመምራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ (Honorary Degree of Humane Letters (DHLitt) የሰጣቸው መሆኑ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ዶ/ር ኢሌኒ ሰሞኑን የዓለም አቀፍ ሰላምና ልማት ማዕከል ተብሎ ይጠራ በነበረው ድርጅት አማካኝነት በድብቅ በተዘጋጀ የበይነመረብ ስብሰባ ላይ ሙያዊነትን ያልጠበቀ፣ አድሏዊ፣ የአንድን ቡድን ፍላጎት ብቻ ያንጸባረቀ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ዋና ዋና እሴቶች የሚፃረር ሀሳብን በማራመዳቸው ዩኒቨርሲቲው ለዶ/ር ኢሌኒ የሰጠውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በድጋሚ ሲያጤን እና ሲመረምር መቆየቱ ተገልጿል፡፡

በዚህም መሠረት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1152/2011 አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 4 እና በዩኒቨርሲቲው የሴኔት ደንብ አንቀጽ ቁጥር 6 ንዑስ አንቀጽ 16 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ህዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ለዶ/ር ኢሌኒ ዘውዴ ገ/መድሕን ሰጥቶት የነበረውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ (Honorary Degree of Humane Letters (DHLitt) እንዲሰረዝ መወሰኑን ገልጿል፡፡

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
12.0K views
Ochish/sharhlash
2021-11-30 17:56:10 የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የሚገኙት የአሜሪካ እና እንግሊዝ ኤምባሲዎች ማብራሪያ እንዲሰጡት ጠየቀ!

የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከሰሞኑ ኤምባሲዎቹ በኢትዮጵያ ላይ እየተከተሉ ያሉትን ያልተገባ አካሄድ በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡት በደብዳቤ ጠይቋል፡፡ አላስታየር ማክ ፍይል

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ከ22 በላይ ህጋዊ እውቅና የተቸራቸው ፓርቲዎችን የያዘው የጋራ ምክር ቤቱ ለአምባሳደር ጊታ ፓሲ እና አምባሳደር አላስታየር ማክ ፍይል በስም ጠቅሶ በጻፈው ድብዳቤ አሜሪካና እንግሊዝ በዚህ ወቅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን መቆም ሲገባቸው ለሽብር ቡድኑ በማድላት ከፍተኛ ደባ እየሰሩ ናቸው ሲል ኮንኗል፡፡

የጋራ ምክር ቤቱ በመግለጫው አሜሪካ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች መተዳደሪያ የሚሆነውን የአጎዋ እድል በመሰረዝም ከፍተኛ ጫና ማሳደሯን ጠቅሷል፡፡

የአሜሪካ መንግስት በሰብአዊነት ሰበብ በኢትዮያዊያን መሃከል ልዩነትን በመፍጠርና እርስበርስ መከፋፈል እንዲኖር እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ ከህወሃት ያልተናነሰ በደል ነው ያለው ምክር ቤቱ ድርጊቱን አውግዟል፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኙት የአሜሪካ እና የእንግሊዝ ኤምባሲዎች በከተማዋ ውስጥ ሰላም እንደሌለ በማስመሰል ተደጋጋሚ መግለጫዎችን በማውጣት ሽብር እየፈጠሩ ነው ያለው የጋራ ምክር ቤቱ፤ ኤምባሲዎቹ የሚያወጧቸውን የተቃረኑ መግለጫዎች ቆም ብለው እንዲፈትሹ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የሁለቱም ሃገራት ኤምባሲዎችም ሆኑ መንግስታት ሽብር ከመንዛት እንዲቆጠቡ ያሳሰበው የጋራ ምክር ቤቱ የእኛን የአፍሪካዊያን ጉዳይ እኛው እንድንፈታው ተውልን በማለት መጠየቁንም ምክር ቤቱን ደብዳቤ ዋቢ በማድረግበማድረግ አሻም ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
13.6K views
Ochish/sharhlash
2021-11-30 17:08:08
Picture 1 from YeneTube 2021-11-30 17:08:08
ከተናጠል ተኩስ አቁም እርምጃው በኋላ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ይጣራል ተባለ!

በሚኒስትሮች የተዋቀረው ግብረኃይል ከዚህ በፊት ኢሰመኮ እና ተመድ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ይፋ ባደረጉት ሪፖርት የተሰጡ ምክረ ሀሳቦችን እንደሚያስፈጽም እና በአማራና አፋር ክልሎች ያለውን ሁኔታ እንደሚያጣራ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የሰብዓዊ መብት ክትትል ለማድረግ ከህዳር 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ስራ የገባዉ የሚኒስትሮች ኮሚቴ የፌደራል መንግሥት ከወሰደው የተናጠል ተኩስ አቁም እርምጃ በኋላ የተከሰቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ እንደሚያተኩር የጽሕፈት ቤቱ ፕሬስ ሰክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ገልጸዋል።

ግብረኃይሉ አራት ኮሚቴዎችን ማቋቋሙንም ተናግረዋል፡፡ ኮሚቴዎቹ የምርመራና የሕግ ክትትል ኮሚቴ፣ የስደተኞችና የውስጥ ተፈናቃዮች ጉዳይ ኮሚቴ፣ የጾታዊ ጥቃቶች ጉዳይ ኮሚቴ እና የሀብት አጠቃቀም ኮሜቴ ናቸው፡፡ ቢልለኔ ለውጭ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ግብረኃይሉ በሕግ አግባብ ፍትሀዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ያደርጋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ጋር በታህሳስ ወር ይፋ ያደረጉት የምርመራ ውጤት ጦርነቱ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ከተስፋፋ በኋላ ያለውን አለማካተቱ የሚታወስ ነው።

[@AddisZeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
13.5K views
Ochish/sharhlash
2021-11-30 14:02:44
Picture 1 from YeneTube 2021-11-30 14:02:44
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ!

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡ሚኒስትሩ በነገው እለት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ይወያያሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
15.3K views
Ochish/sharhlash