"YeneTube" Telegram kanali

Telegram kanalining logotibi yenetube — YeneTube
1,312
Kanaldagi mavzular:
Artland
Shegerhive
Ethiopia
Addisababa
Hiking
Marakiconsultancy
Free
Telegram kanalining logotibi yenetube — YeneTube
Kanaldagi mavzular:
Artland
Shegerhive
Ethiopia
Addisababa
Hiking
Marakiconsultancy
Free

"YeneTube" Telegram kanali

Kanal manzili: @yenetube
Toifalar: Kattalashtirilmagan
Obunachilar: 165,242 (Yangilash sanasi: 2021-12-09)
Kanalning ta’rifi

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Sharhlar

Izohni e’lon qilish uchun tizimga kirish zarur.Oxirgi xabar 7

2021-12-01 19:26:27 ሰበር ዜና!

ላስታ ላሊበላ በኢትዮጵያ ጦር ቁጥጥር ውስጥ ገባች!

የጋሸናን ግንባር ምሽጎች ሰብረው የአሸባሪውን አከርካሪ የሰበሩት የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ታሪካዊቷን የላስታ ላሊበላ ከተማንና የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ተቆጣጠሩ።

በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙባትን የላሊበላ ከተማንና ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያውን ለመቆጣጠር የተቻለው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት በየግንባሩ የተጀመረው ማጥቃት ውጤት ለማስመዝገብ በመቻሉ ነው።

ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ የላስታ ላሊበላን አካባቢ በማጽዳት የሰቆጣ ከተማን ለመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሡ ነው።

ራሳቸውን በጠላት እንዳላስደፈሩት የግዳንና የራያ ወረዳዎች ሁሉ ቀሪዎቹ በወረራ ሥር የሚነገኙ የዋግ ሕምራ፣ የሰሜንና የደቡብ ወሎ ሕዝብ፣ ከጀግኖቹ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ጠላትን እንዲደመስስና ነጻነቱን እንዲያስከብር መንግሥት ጥሪ ያቀርባል።

[የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት]
@YeneTube @FikerAssefa
12.4K viewsedited  
Ochish/sharhlash
2021-12-01 19:21:57 ባለፉት 3 ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ ቡድን የተከፈቱ አካውንቶች ናቸው ተባለ፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በወጣው መግለጫ 122,000 ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ ብሏል፡፡ከእነዚህ የሀሰት መረጃ ከሚያሰራጩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ ቡድን የተከፈቱ መሆናቸውን አጀንሲው ተነግሯል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የህውሐት ቡድን በ2013 ዓ.ም ጦርነት በከፈተበት ህዳር ወር ብቻ 17,000 የሚሆኑ ሀሰተኛ የቲዊተር አካውንቶችም በዲጂታል ወያኔ ቡድን ተከፍተው ነበር ተብሏል፡፡የኤጀንሲው የግልጽ ምንጭ መረጃ ኦፕሬሽን ማዕከል ኃላፊ የሆኑት አቶ አሸናፊ ኃይሉ በቡድኑ በተከፈቱ ሀሰተኛ አካውንቶች በአንድ ቀን ብቻ 25,000 የሚደርሱ መልዕክቶች በቲውተር ምህዳሩ ላይ ይሰራጩ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡

የህወሐት ቡድን እነዚህን ሁሉ ዘመቻዎች አድርጎ አልሳካ ሲለው ለሽብር ተግባር ተባባሪ ከሆኑ ሃገራት እገዛ በማግኘት እንዲሁም አስቀድመው አስርገዉ ያስገቧቸዉን ሰዎች በመጠቀም ከእውነታ ውጪ የሆኑ ዘገባዎችን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ እየሰሩ እንደሚገኙ ኤጀንሲው እወቁት ብሏል፡፡

ተዋቂዎቹ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችም ከጥፋት ቡድኑ ጋር የተያያዙ ወይም ለቡድኑ ይጠቅማሉ ያሏቸውን ይዘቶች በፕላትፎርማቸው ላይ እንዲኖሩ ወይም እንዲቆዩ ከመፍቀድ ባለፈ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆኑ ለሌሎች አካላት በስፋት ያሰራጩላቸው(Suggest)ያደርጉላቸው እንደነበረም ሀላፊው አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል የሀገርን አንድነት ወይም ኢትዮጵያዊነትን የሚያቀነቅኑ አካውንቶችን የመዝጋትና መረጃዎቻቸው እንዳይሰራጩ የማድረግ እንዲሁም አንዳንድ አካውንቶችን መረጃ እንዳይለጥፉ ከማድረግም ባለፈ ለተለያየ ጊዜ ሲዘጉ እንደነበር አቶ አሸናፊ አብራርተዋል፡፡

[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
12.0K views
Ochish/sharhlash
2021-12-01 17:35:20
Picture 1 from YeneTube 2021-12-01 17:35:20
ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ለ 13 አመታት ሲጠቀምበት የነበረውን የንግድ ስያሜ እና የንግድ ምልክት ሊቀይር መሆኑን ገለፀ።

ባንኩ ካለበት የእድገት ደረጃ አና ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር ለመሄድ ቅየራውን አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ተፈሪ መኮንን ገልጸዋል።

Viia Capital
@YeneTube @FikerAssefa
13.2K views
Ochish/sharhlash
2021-12-01 16:57:58 በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ ሰብሳቢነት በተመራውና በአሸባሪነት የተፈረጀውን ሕወሃት ለመደገፍ በተካሄደው ስብሰባ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች በአሜሪካ ሀገር ምርመራ ተካሂዶ ክስ እንዲመሰረትባቸው ተጠየቀ፡፡

ህወሃትን ለመደገፍና በህዝብ የተመረጠን መንግስት ከስልጣን ለማውረድ በተጠራው ስብሰባ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች ምርመራ እንዲካድባቸውና ክስ እንዲመሰረትባቸው የጠየቁት በአሜሪካ አገር ያሉ አራት የትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ናቸው፡፡

ብርሃኔ ገብረክርስቶ፣ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ፣ ዶ/ር እሌኒ ገ/መድህን፣ አቶ በቀለ ገለታ፣ አቶ ታደሰ ውሂብ ፣ አቶ ኩላሂ ጃለታ፣ ዶናልድ ይማማቶን ጨምሮ 14 ግለሰቦች ናቸው በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶቹ ምርመራ ተደርጎባቸው ክስ እንዲመሰረትባቸው የተጠየቀባቸው፡፡ግሰለቦቹ እንዲከሰሱ የሚጠይቀውን ማመልከቻ ድርጅቶቹ ለአሜሪካ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማቅረባቸው ተሰምቷል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በግለሰቦቹ ላይ ምርመራ እንዲካሄድባቸውና ክስ እንዲመሰረትባቸው ያበቃቸው ምክንያት በደብዳቤያቸው ላይ የጠቀሱ ሲሆን ፣ በአሜሪካ መንግስት በውጪ ጉዳይ ፖሊስ እና ብሔራዊ ጥቅም ላይ የተፈፀመው ጉዳቶችን አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ረጅም ዓመት የዘለቀ ወዳጅ ሀገር መሆናቸወን የጠቀሰው ማመልከቻው አሜሪካ ወዳጅ በሆነችባቸው አገሮች ውስጥ በህጋዊ መንገድ የተመረጠን መንግስት በሀይል ለማውረድ ማሴር ህገ-ወጥ መሆኑን አንቀፅ ጠቅሰው አመልክቷል፡፡

በማመልከቻው ስማቸው የተጠቀሰው ግለሰቦችም ይህን የአሜሪካ ህግ በሚጥስ መልኩ ተሳትፈው መገኘታቸውንም አስረድተዋል፡፡ይህም በመሆኑ በአሜሪካ መንግስትና በውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ እንዲሁም በኢትዮጵያ በሚገኘው ኤምባሲዋ ላይ ጉዳት ደርሷል ሲሉ ድርጅቶቹ አመልክተዋል፡፡ድርጅቶቹ በማመልከቻቸው ሕወሃት በኢትዮጵያ ያደረገውንና እያደረሰ ያለውንም ጉዳት ዘርዝረዋል።

[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
13.7K views
Ochish/sharhlash
2021-12-01 16:44:02
Picture 1 from YeneTube 2021-12-01 16:44:02
በቡራዩ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ለኦነግ ሸኔ ሊተላለፍ የነበረ ለፀጥታ አካላት ብቻ የተፈቀደላቸው ቀበቶና የመሣሪያ ጥይቶች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ልዩ ቦታ ገፈርሳ ኖኖ ተብሎ የሚጠራ ቦታ መነሻ አዲስ አበባ ጎጀም በረንዳ ያደረገ ለሸኔ ወደ ምስራቅ ወለጋና ምዕራብ ወለጋ ሊላክ የነበረ 2656 ለፀጥታ አካላት ብቻ የተፈቀደላቸው ቀበቶና 4143 የክለሽንኮቪ ጥይቶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለፀ።

ከህገወጥ ቀበቶና ጥይቶቹ ጋርም 5 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥሪ መዋላቸውን በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ፖሊሲ መምሪያ የወረዳ 1 ፖሊስ ፍትህ መስጠት የሥራ ሂደት ባለቤት ሳጅን ሙሉነህ ቃናዓ ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
12.9K views
Ochish/sharhlash
2021-12-01 15:54:11
Picture 1 from YeneTube 2021-12-01 15:54:11
እንደ ቀድሞ ቅኝ ገዥዎቻቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ የጉዞ ገደብ ያደረጉ የአፍሪካ ሀገራት ዉሳኔ ያሳዝናል ሲሉ ራማፎሳ ተናገሩ!

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሀገራት የሚደረገውን ጉዞ በመገደብ የምዕራባውያን ድርጊት የተከተሉ የአፍሪካ ሀገራትን ተቃዉመዋል፡፡ራማፎሳ የሚያሳዝን ዉሳኔ ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ኦሚክሮን በደቡብ አፍሪካ መገኘቱን ተከትሎ እንደ ቀድሞ ቅኝ ገዥዎቻቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ ጉዞን የከለከሉ የአፍሪካ ሀገራት እንዲህ ዓይነት ዉሳኔ ባይወስዱ ይመረጥ ነበር ሲሉ ራማፎሳ ተናግረዋል፡፡በርግጥ እኔንም ያሳስበኛል ደግሞም ለእነሱ አክብሮት አለኝ ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

አፍሪካን ለመዝጋት በጣም ፈጣን እንደነበሩት እንደቀድሞ ቅኝ ገዥዎቻችን ምላሽ ባይሰጡን ኖሮ ዉይይትን እንመርጥ ነበር ሲሉ ራማፎሳ ተናግረዋል፡፡ሩዋንዳ፣ ሲሸልስ፣ ሞሪሸስ፣ ግብፅ እና አንጎላ ድንበራቸውን ወደ ደቡብ አፍሪካ ሀገራት ከዘጉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

የኦሚክሮን አዲስ ልዉጥ ቫይረስ በደቡብ አፍሪካ መገኘቱን የአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ካደረገ በኃላ በበርካታ ሀገራት ዉስጥ ተጠቂዎች እየተገኙ ይገኛል፡፡ደቡብ አፍሪካ በራሷ እና በአጎራባች ሀገራት ላይ የተጣለውን የጉዞ ክልከላ ፍትሃዊ ያልሆነ እና ሳይንስን መሰረት ያላደረገ ስትል ታወግዛለች።

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
13.7K views
Ochish/sharhlash
2021-12-01 12:09:50
Picture 1 from YeneTube 2021-12-01 12:09:50
የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ማስገባቱ ተገለፀ!

በሀገሪቱ ያለውን ገበያ ዋጋ ለማረጋጋት የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን 8 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለማስገባት አቅዶ በመጀመሪያው ዙር 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ማስገባቱ ተገለፀ።ከውጭ ሀገር ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ ተገዝቶ የገባው ይህ ስንዴ በአምስት ማዕከላት ማለትም በአዲስ አበባ፣ በሻሸመኔ፣ በባህርዳር፣ በአዳማ እና ድሬዳዋ በሚገኙ ማሰራጫ ማዕከላት ይሰራጫልም ሲሉ የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አቻ ደምሴ አስታውቀዋል። በተለያዩ ዳቦ ቤቶች የሚታየውን የዋጋ ጭማሬ እና የዱቄት እጥረት በመቅረፍ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ይደረጋልም ብለዋል።በሚቀጥሉት 15 ቀናት ስርጭቱ በማዕከላቶቹ የሚከናወን ሲሆን የሚሰራጨው ስንዴ በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋሉን ቁጥጥር ይደረጋልም ተብሏል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
15.2K viewsedited  
Ochish/sharhlash
2021-12-01 09:54:04 በተያያዘ ዜና በወረኢሉ ግንባር

-ኢንቆፍቱ፣
-አቃስታ፣
-ወረኢሉ ከተሞችን የኢትዮጵያ ጦር ተቆጣጥሯል።

በሸዋ ግንባር

መዘዞ፣
ሞላሌ፣
ሸዋሮቢት ነፃ ወጥተዋል።

በምስራቅ ግንባር በርካታ አካባቢዎች ከጠላት ነፃ በማድረግ መልሶ የማደራጀት ስራ ተጀምሯል።

በመሆኑም እየሸሸ ያለውን የህወሓት ወራሪ ቡድን ህዝቡ ተደራጅቶ እንዲደመስስ ጥሪ ተላልፏል።

@YeneTube @FikerAssefa
15.6K viewsedited  
Ochish/sharhlash
2021-12-01 09:39:41
Picture 1 from YeneTube 2021-12-01 09:39:41
ሰበር ዜና!

ጋሸና በኢትዮጵያ ጦር ቁጥጥር ስር ዋለ!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ የጋሸና፣አርቢትና ሌሎች የትግሬ ወራሪ ኃይልን ምሽግ ደርምሶ ወደ ወልዲያ እየገሰገሰ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ገልፆአል።

በሸዋና በደቡብ ወሎም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ ተጋድሎ በርካታ ቦታዎች ነፃ መውጣታቸው ተገልፆአል።

@YeneTube @FikerAssefa
15.2K viewsedited  
Ochish/sharhlash