Get Mystery Box with random crypto!

ሳፋየር አዲስ ሆቴል መታሸጉ ተሰማ! አትላስ አካባቢ የሚገኘው ‹‹ሳፋየር አዲስ ሆቴል›› በግልጽ | YeneTube

ሳፋየር አዲስ ሆቴል መታሸጉ ተሰማ!

አትላስ አካባቢ የሚገኘው ‹‹ሳፋየር አዲስ ሆቴል›› በግልጽ ባልተነገረ ምክንያት መታሸጉ ተሰማ፡፡ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሆቴሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮናስ ወርቁ፣ሳፋየር አዲስ ከሐሙስ ኅዳር 23 ቀን 2014 ዓም ጀምሮ መታሸጉን ያረጋገጡ ሲሆን፣ ሆቴሉ በምን ምክንያት እንደታሸገ ከመንግሥት አካላት የተደረገላቸው ገለጻ እንደሌለ አስታውቀዋል፡፡ባለፉት ሦስትና አራት ወራት ውስጥ ሆቴሉ ለአራት ጊዜ ፍተሻ እንደተደረገበትና የመጨረሻው ፍተሻ ከመታሸጉ ሁለት ቀናት በፊት ማክሰኞ ኅዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም. እንደነበር አቶ ዮናስ ተናግረዋል፡፡‹‹በሁሉም ፍተሻ ምንም ነገር አልተገኘም፤›› ያሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ ይኼንን የሚያረጋግጥ ፊርማ የፈተሹት አካላትና የሆቴሉ አስተዳዳር መፈረማቸውን አክለው ገልጸዋል፡፡

አቶ ዮናስ ሆቴሉ ከመታሸጉ በፊት ማስጠንቀቂያ አለመሰጠቱን ተናግረው፣ አሁንም ቢሆን ከመንግሥት በኩል ምክንያቱ እስከሚነገራቸው እየጠበቁ መሆኑን አስረድተዋል፡፡በፍተሻው ጊዜ ምንም ስላልተገኘባቸው በቶሎ ይከፈታል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ዋና ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡ሳፋየር አዲስ ሆቴልን ያሸገው የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በበኩሉ፣ ዕምርጃው የተወሰደው በወረዳው በተዋቀረው ግብረ ኃይል አማካኝነት ጥናት ተደርጎ መሆኑን አስታውቋል፡፡ሪፖርተር ያነጋገራቸው የወረዳው ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ጀባሞ፣ሳፋየር አዲስ የታሸገበትን ምክንያት ከመናገር ተቆጥበው፣ወረዳው ውስጥ ‹‹በወቅታዊ ሁኔታ›› ዕርምጃ የተወሰደባቸው አብዛኞቹ ሆቴሎች ‹‹በአሸባሪነት ከተፈረጀው ሕወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው፣ እንዲሁም ድጋፍ ያደርጋሉ›› ተብሎ በመጠርጠራቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/24000

@YeneTube