Get Mystery Box with random crypto!

የህወሐት ቡድን በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በርካታ የማምረቻ ተቋማትን አውድሟል- የኢንዱስትሪ ሚኒ | YeneTube

የህወሐት ቡድን በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በርካታ የማምረቻ ተቋማትን አውድሟል- የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

አሸባሪው የማፍያ ቡድን በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ የማምረቻ ተቋማትን ማውደሙን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሰረተ ልማትና ግብአት አቅርቦት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ ገልጸዋል፡፡ይህ ማፍያ ቡድን በማምረቻ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ማሽኖችን ጭኖ በመውሰድና የቀሩትን አገልግሎት አንዳይሰጡ አድርጎ አውድሟል፣ የንግድ ተቋማትን ዘርፏል ብለዋል አቶ ሺሰማ፡፡

አሸባሪ ቡድኑ በዚህ እኩይ ተግባሩ በአማራ ክልል የሚገኙ 10 የምግብና ምግብ ነክ አምራች ተቋማትን፣ 11 የቆዳና ጨርቃጨርቅ፣3 የብረታብርት፣ 11 የግብርና ማቀነባበሪያ እንዲሁም 10 የኬሚካል አምራች ተቋማትን አውድሟል ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም በአፋር ክልል 4 የማምረቻ ተቋማትን ማውደሙን የጠቀሱት ሚኒስር ዴኤታው የወደሙ አምራች ድርጅቶችን ወደ ቀድሞ የማምረት ተግባራቸው ለማስገባት የደረሰውን ጉዳት የሚያጠና ቡድን ወደ ስፍራው እንደሚላክም ገልጸዋል፡፡

የተቋማቱ የጉዳት መጠን ከተለየ በኋላ ከጉዳታቸው አገግመው ወደ ማምረት ሂደታቸው እንዲገቡ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ልዩ ድጋፍ በማድረግ በተለየ ትኩረት እንደሚሰራ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa