Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች ለ2 ሚሊዮን ዕርዳታ ፈላጊዎች | YeneTube

የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች ለ2 ሚሊዮን ዕርዳታ ፈላጊዎች 28 ሺህ ሜትሪክ ቶን አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እንደመደበ እና ለጋሸና እና ላሊበላ ተረጅዎች ደም 5 ሺህ ኩንታል ምግብ እንደላከ የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢልለኔ ሥዩም በዛሬው መግለጫቸው አስታውቀዋል። በአፋር ክልልም ከ1.3 ሚሊዮን ዕርዳታ ፈላጊ ሕዝብ ውስጥ ለተወሰነው ዕርዳታ እየተከፋፈለ እንደሆነ በመግለጫው ላይ ተገልጧል። ቢልለኔ ጨምረውም፣ ሕወሃት 900 ዕርዳታ ጫኝ የረድዔት ድርጅቶች ካሚዮኖችን ነጥቆ ታጣቂዎቹን ከቦታ ቦታ ሲያጓጉዝባቸው፣ አንዳንድ የውጭ መንግሥታት ዝምታን መርጠዋል በማለትም ወቅሰዋል።

@YeneTube @FikerAssefa