Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የመሰረታዊ ፍጆታ ምርት ለማቅረብና የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት 5 | YeneTube

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የመሰረታዊ ፍጆታ ምርት ለማቅረብና የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት 500 ሚሊዮን ብር ለሪቮልቪንግ ፈንድ ፈቀደ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው በአንደኛ ዓመት ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው የመሰረታዊ ፍጆታ ምርት ለማቅረብና የእህል የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት ከዚህ ቀደም ካደረገው ብድር በተጨማሪ 500ሚሊዮን ብር ለሪቮልቪንግ ፈንድ ፈቅዷል።የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ህዳር 20 ቀን 2014 ዓ.ም በአንደኛ ዓመት ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

ከውሳኔዎቹም መካከል፤
1. ሆፕ ፎር ችልድረን ኦርጋናይዜሽ አውስትራሊያ ሊምትድ የተባለው ግብረሰናይ ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 01 ክልል ውስጥ በ600 ሚልየን ብር የመሬት አጠቃቀሙ ባለ ብዙ አገልግሎት የሆነ ቦታ ላይ ወላጅ አልባ እና ደጋፊ ለሌላቸው ሕጻናት የልህቀት ማእከል ለመገንባት በመሬት ልማትና አስተዳደር የቀረበውን የውሳኔ መነሻ ተቋሙ ስራውን አጠናቆ ወደ ተግባር ሲገባ የሚሰጠውን አገራ ዊፋይዳ ከግምት ውስጥ በማስገባት የተዘጋጀው ቦታ ከዚህቀደም መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት በሚስተናገዱበት መሰረት እንዲስተናገዱ ካቢኔው ውሳኔ አሳልፏል ፡፡

2. በሱማሌ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በዝናብ እጥረት ምክንያት በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች እየደረሰ ያለውን ጉዳት መነሻ በማድረግ ውይይት አድርጎ የ100,000,000.00( አንድ መቶ ሚልየን ብር ) የአይነት ድጋፍ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በዚህ መሰረት የ50,000,000.00 ( ሃምሳ ሚልየን ብር ) ለሱማሌ ክልል እና የ50,000,000.00 ( ሃምሳ ሚልየን ብር ) ለቦረና ዞን የአይነት ድጋፍ እንዲደረግ እና ይህንን ተግባር የሚያስፈጽሙ የካቢኔ አባላት ኮሚቴ ሰይሟል ፡፡

3. የከተማ አስተዳደሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የከተማ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል የመሰረታዊ የፍጆታ እቃ የሚውል የሸማቾች የሕብረት ስራ ማኀበራት ያለባቸውን የካፒታል እጥረት ለመቅረፍ ፣ የመሰረታዊ ፍጆታ ምርት ለማቅረብ እና የእሕል የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት ይቻል ዘንድ ከተማ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም ካደረገው 500,000,000.00 ( የአምስት መቶ ሚልየን ብር ) ብድር ድጎማ በተጨማሪ ለሸማቾች ህብረት ሥራ ዩኒየኖች የግብርና ምርቶች የሚያቀርቡበት ብድር ማቅረብ አስፈላጊ በመሆኑ ለጤፍ እና ለስንዴ ግዢየ ሚውል 500,000,000.00 ( የአምስት መቶ ሚልየን ብር ) ለሪቮልቪንግ ፈንድ የፈቀደ ሲሆን የግዢ ሂደቱም የሸማቾች ሕብረት ስራ ማኀበራት ግዢውን በቀጥታ ከአምራች መሰረታዊ ማኀበራት እንዲፈጸም ካቢኔው ወስኗል፡፡

[Asham TV]
@YeneTube @FikerAssefa