Get Mystery Box with random crypto!

ህወሓት የጅምላ ግድያ መፈጸሙን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የዓለም አቀፍ ግ | YeneTube

ህወሓት የጅምላ ግድያ መፈጸሙን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የዓለም አቀፍ ግንኙትና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ ቢለኔ ስዩም ገለጹ።

ኃላፊዋ ለውጭ አገር መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ማብራሪያ ህወሓት በሁለቱ ክልሎች ወረራ በመፈጸም ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን ገልጸዋል።በተለይም በአማራ ክልል አንጾኪያ እና ጋሸና የጅምላ መቃብር መገኘቱን በጋዜጣዊ መግለጫቸው አስረድተዋል።ከዚህ ባለፈም በአማራ እና አፋር ክልሎች በንጹሃን ላይ ግድያ መፈጸሙን የጠቀሱት ኃላፊዋ፥ ሴቶችን መድፈሩን እና ከፍተኛ የንብረት ውድመት ማድረሱንም ገልጸዋል፡፡

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa