Get Mystery Box with random crypto!

የቱሩዝም ሚኒስቴር ዲያስፖራዎችን ለመቀበል ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ! በቱሪዝም መስኩ የተሰማሩ | YeneTube

የቱሩዝም ሚኒስቴር ዲያስፖራዎችን ለመቀበል ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ!

በቱሪዝም መስኩ የተሰማሩ ተዋንያን በሚሰጡት አገልግሎት ላይ 30 በመቶ ቅናሽ ሊያደርጉ መሆኑ ተገለጸ፡፡የቱሪዝም ሚንስቴር ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መንግት ለ1 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደሀገራቸው እንዲመጡ ጥሪ ማድረጉን ተከትሎ ቱሪዝም ሚንስቴር ምቹ መደላድሎችን ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ሆቴሎች፣ የተሽከርካሪ አከራዮች፣ አስጎብኚዎች እና ሌሎች የዘርፋ ተዋንያን ከሚሰጡት አገልግሎት ላይ የ30 በመቶ የክፍ ቅናሽ ለማድረግ መወሰናቸውን የቱሪዝም ሚንስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደሀገራቸው መምጣታቸው እና መጎብኘታቸው ለሀገሪቱ ከሚያመጣው ምጣኔ ሀብታዊ እገዛ ባሻገር እውነታውን ለአለም ለማስረዳት እንደሚያግዝ ተገልጿል።የቱሪዝም ዘርፉን በዘላቂነት እንዲያሰራራ ለማድረግም ዘላቂ ስትራቴጂ ተነድፎ ይሰራልም ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa