Get Mystery Box with random crypto!

ተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ተመቷል በሚል በድጋሜ የሚሰራጨው መረጃ የሐሰት መሆኑ ተገለጸ! | YeneTube

ተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ተመቷል በሚል በድጋሜ የሚሰራጨው መረጃ የሐሰት መሆኑ ተገለጸ!

የተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ በመንግስት ተመቷል በሚል በሽብርተኛው የህወሓት ቡድንና በአቀንቃኞቹ የሚናፈሰው ወሬ ሐሰት መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።ከዚህ ቀደምም ግድቡ ተመቷል በሚል በጥፋት ቡድኑ ተመሳሳይ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ተሰራጭቶ እንደነበር ይታወሳል።

በመንግስት የተመታው የተከዜ ግድብ ሳይሆን ተከዜን ተሻግሮ ወረራ የፈፀመው የሽብር ቡድኑ ነው።ይሁንና የተከዜ ግድብ ባለፈው ክረምት ሙሉ በመሆኑ ውሃው እንዲፈስ በማድረግ የሀሰት ፕሮፓጋንዳውን እውነት ለማስመሰል ጥረት ሊያደርግ እንደሚጥር ይገመታል።የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ሙያተኛ ባልሆኑ ሰዎች፣ ከታለመለት ዓላማ ውጪ እንዲሰራ ከተደረገ ከፍተኛ መጠን ያለው ጉዳት ሊደርስበት እንደሚችል ይታመናል።

በመሆኑም የሽብር ቡድኑ ህዝብን ለማሸበርና ዓለም አቀፍ ትኩረት ለመሳብ ውሃውን ሊለቅ ስለሚችል በግድቡ የታችኛው ተፋሰስ አካባቢ በተለይም በጣንቋ አበርገሌ፣ በጠለምት፣ በቃፍታ ሁመራ፣ በጠገዴ፣ በአበርገሌና በወልቃይት አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተቋሙ አሳስበዋል።መረጃ የደረሳችሁ የህብረተሰብ ክፍሎች መልዕክቱን በማስተላለፍ ትብብር እንድታደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

የተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሙሉ በሙሉ በሽብርተኛ ቡድኑ ቁጥጥር ስር ከመዋሉ በፊት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ መለዋወጫ ተሟልቶለትና ከሁለት መቶ በርሜል በላይ የተርባይን ዘይት አቅርቦት ቀርቦለት በጥሩ ሁኔታ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነበር ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ገልጾአል።

(ኢ ፕ ድ)
@YeneTube @FikerAssefa