Get Mystery Box with random crypto!

ትዊተር ኩባንያ 'በቃ!' በሚል መሪ ቃል የምዕራቡ ዓለም ሀገራት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገ | YeneTube

ትዊተር ኩባንያ "በቃ!" በሚል መሪ ቃል የምዕራቡ ዓለም ሀገራት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በማውገዝ የትዊተር ዘመቻ የሚያደርጉ የኢትዮጵያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የትዊተር ገጾችን እንደዘጋ ተሰምቷል። ኩባንያው ስንት የትዊተር ገጾችን እንደዘጋ ግን ገና አልታወቀም። የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤትም ትዊተር ኩባንያ አፍቃሬ-ኢትዮጵያ የሆኑ ድምጾችን እያፈነ ነው ብሎ እንደሚያምን ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የፕሬስ ሴክሬታሪ ቢልለኔ ሥዩም ተናግረዋል። የሕወሃት ደጋፊዎች በኩባንያ ውስጥ በብዛት እንደሚገኙ መንግሥት ለኩባንያው ማሳወቁንም ቢልለኔ አስታውቀዋል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa