Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የሚገኙት የአሜሪካ እና እንግሊዝ ኤምባ | YeneTube

የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የሚገኙት የአሜሪካ እና እንግሊዝ ኤምባሲዎች ማብራሪያ እንዲሰጡት ጠየቀ!

የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከሰሞኑ ኤምባሲዎቹ በኢትዮጵያ ላይ እየተከተሉ ያሉትን ያልተገባ አካሄድ በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡት በደብዳቤ ጠይቋል፡፡ አላስታየር ማክ ፍይል

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ከ22 በላይ ህጋዊ እውቅና የተቸራቸው ፓርቲዎችን የያዘው የጋራ ምክር ቤቱ ለአምባሳደር ጊታ ፓሲ እና አምባሳደር አላስታየር ማክ ፍይል በስም ጠቅሶ በጻፈው ድብዳቤ አሜሪካና እንግሊዝ በዚህ ወቅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን መቆም ሲገባቸው ለሽብር ቡድኑ በማድላት ከፍተኛ ደባ እየሰሩ ናቸው ሲል ኮንኗል፡፡

የጋራ ምክር ቤቱ በመግለጫው አሜሪካ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች መተዳደሪያ የሚሆነውን የአጎዋ እድል በመሰረዝም ከፍተኛ ጫና ማሳደሯን ጠቅሷል፡፡

የአሜሪካ መንግስት በሰብአዊነት ሰበብ በኢትዮያዊያን መሃከል ልዩነትን በመፍጠርና እርስበርስ መከፋፈል እንዲኖር እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ ከህወሃት ያልተናነሰ በደል ነው ያለው ምክር ቤቱ ድርጊቱን አውግዟል፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኙት የአሜሪካ እና የእንግሊዝ ኤምባሲዎች በከተማዋ ውስጥ ሰላም እንደሌለ በማስመሰል ተደጋጋሚ መግለጫዎችን በማውጣት ሽብር እየፈጠሩ ነው ያለው የጋራ ምክር ቤቱ፤ ኤምባሲዎቹ የሚያወጧቸውን የተቃረኑ መግለጫዎች ቆም ብለው እንዲፈትሹ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የሁለቱም ሃገራት ኤምባሲዎችም ሆኑ መንግስታት ሽብር ከመንዛት እንዲቆጠቡ ያሳሰበው የጋራ ምክር ቤቱ የእኛን የአፍሪካዊያን ጉዳይ እኛው እንድንፈታው ተውልን በማለት መጠየቁንም ምክር ቤቱን ደብዳቤ ዋቢ በማድረግበማድረግ አሻም ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa