Get Mystery Box with random crypto!

ከተናጠል ተኩስ አቁም እርምጃው በኋላ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ይጣራል ተባለ! በሚኒስትሮች | YeneTube

ከተናጠል ተኩስ አቁም እርምጃው በኋላ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ይጣራል ተባለ!

በሚኒስትሮች የተዋቀረው ግብረኃይል ከዚህ በፊት ኢሰመኮ እና ተመድ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ይፋ ባደረጉት ሪፖርት የተሰጡ ምክረ ሀሳቦችን እንደሚያስፈጽም እና በአማራና አፋር ክልሎች ያለውን ሁኔታ እንደሚያጣራ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የሰብዓዊ መብት ክትትል ለማድረግ ከህዳር 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ስራ የገባዉ የሚኒስትሮች ኮሚቴ የፌደራል መንግሥት ከወሰደው የተናጠል ተኩስ አቁም እርምጃ በኋላ የተከሰቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ እንደሚያተኩር የጽሕፈት ቤቱ ፕሬስ ሰክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ገልጸዋል።

ግብረኃይሉ አራት ኮሚቴዎችን ማቋቋሙንም ተናግረዋል፡፡ ኮሚቴዎቹ የምርመራና የሕግ ክትትል ኮሚቴ፣ የስደተኞችና የውስጥ ተፈናቃዮች ጉዳይ ኮሚቴ፣ የጾታዊ ጥቃቶች ጉዳይ ኮሚቴ እና የሀብት አጠቃቀም ኮሜቴ ናቸው፡፡ ቢልለኔ ለውጭ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ግብረኃይሉ በሕግ አግባብ ፍትሀዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ያደርጋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ጋር በታህሳስ ወር ይፋ ያደረጉት የምርመራ ውጤት ጦርነቱ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ከተስፋፋ በኋላ ያለውን አለማካተቱ የሚታወስ ነው።

[@AddisZeybe]
@YeneTube @FikerAssefa