Get Mystery Box with random crypto!

በቦረና በድርቅ ለተጎዱ እንስሳት የሚውል መኖ በ52 ሔክታር መሬት ላይ እየለማ መሆኑ ተነገረ! ለ | YeneTube

በቦረና በድርቅ ለተጎዱ እንስሳት የሚውል መኖ በ52 ሔክታር መሬት ላይ እየለማ መሆኑ ተነገረ!

ለተከሰተው መጠነ ሰፊ ድርቅ ድጋፍ የሚያሰባስብ ኮሚቴ ሥራ መጀመሩ ተሰምቷል።በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በተከሰተው መጠነ ሰፊ ድርቅ እየደረሰ የሚገኘውን የቁም እንስሳት ዕልቂት ለመከላከል፣ ለተጎዱ እንስሳት የሚያገለግል መኖ በ52 ሔክታር መሬት ላይ እየለማ መሆኑ ተነገረ፡፡

በኦሮሚያ፣ መስኖና አርብቶ አደር ቢሮ የጥናትና ምርምር ዳይሬክተር አቶ ከተማ ኡርጋ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የድርቁ ሁኔታ ካለው አስከፊነት አኳያ ሰፊ ጉዳት ሳያደርስ እንዴት መድረስ ይቻላል የሚለውን ከክልሉ ግብርና ቢሮ፣ ከውኃና ኢነርጂ ቢሮ፣ ከኦሮሚያ አደጋ ሥጋትና መልሶ ማቋቋም ኮሚሽንና ሌሎች አካላት ጋር ከአጭር እስከ ረጅም ጊዜ የታለመ ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa