Get Mystery Box with random crypto!

እስራኤል 3 ሺህ ቤተ እስራኤላዊያን ከኢትዮጵያ ልትቀበል መሆኑን አሶሼትድ ፕሬስ(ኤፒ) ዘግቧል፡፡ | YeneTube

እስራኤል 3 ሺህ ቤተ እስራኤላዊያን ከኢትዮጵያ ልትቀበል መሆኑን አሶሼትድ ፕሬስ(ኤፒ) ዘግቧል፡፡

እስራኤል መንግስት እንዳስታወቀው ላለፉት 25 ዓመት ወደ ቴልአቪቭ ለማቅናት ሲጠባበቁ የነበሩ 3 ሺህ ዜጎችን ለመቀበል ተወስኗል፡፡ሀገሪቱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በፈረንጆቹ 2015 በኢትዮጵያ ይኖሩ የነበሩ 6 ሺህ ቤተ እስራኤላዊያንን ለመቀበል በወሰነው መሰረት መሆኑን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡

የሀገሪቱ ስደተኞች ሚኒስትር ፕኒና ታማኖ እንዳሉት እስራኤል ቤተ እስራኤላዊያንን ከኢትዮጵያ ወደ ሀገሯ ማስገባት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በድምሩ 140 ሺህ ዜጎችን ቴልአቪቭ ደርሰዋል፡፡ይሁንና አሁንም በርካታ ቁጥር ያላቸው ቤተ እስራኤላዊያን በኢትዮጵያ ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው እየኖሩ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሯ 3 ሺህ ዜጎች እንዲገቡ መወሰኑን መልካም ነው ብለዋል፡፡

የቤተ እስራኤላዊያን ማህበር ሊቀመንበር በበኩሉ ውሳኔው ጥሩ መሆኑን ገልጾ ወደ ቴልአቪቭ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው ዜጎች መቼ እና እንዴት የሚለው አብሮ አለመወሰኑን ጠቁሟል፡፡የአሁኑ የእስራኤል መንግስት ውሳኔ ከ25 ዓመታት በላይ በከፋ ችግር ውስጥ ሆነው ሲጠባበቁ ለነበሩ ዜጎች ጥሩ ዜና መሆኑን ገልጾ አሁንም በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በእስራኤል ካሉ ቤተሰቦቻቸው ጋር ለመቀላቀል በመጠባበቅ ላይ ናቸው ብሏል፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa