Get Mystery Box with random crypto!

ለህወሓት የተሰለፉ ሁሉ እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ! በግን | YeneTube

ለህወሓት የተሰለፉ ሁሉ እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ!

በግንባር ተገኝተው በአንደኛው የጦር ግንባር የመጨረሻ ዕቅድ ላይ የመከሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአጠረ ጊዜና በአነስተኛ መሥዋዕትነት የኢትዮጵያ ድል የሚረጋገጥበትን መመሪያ ሰጥተዋል። ሠራዊቱ በከፍተኛ ሞራል ላይ እንደሚገኝና ጠላትም እየተሸነፈ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በተደናበረ ዕቅድ የገባው ጠላት ተደናብሮ መውጣት እንደማይችል ተናግረዋል።

ለህወሓት ዓላማ የተሰለፉ ሁሉ እጃቸውን በመስጠት ራሳቸውን እንዲያተርፉ፣ የትግራይ ወላጆችም ልጆቻችን የት ደረሱ ብለው እንዲጠይቁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።የኢትዮጵያ ፍላጎት ሰላምና ልማት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደዚህ ጦርነት የገባነው ተገድደን ነው ብለዋል። ማሸነፋችን ግን አይቀሬ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa