Get Mystery Box with random crypto!

'የተቀመጠው የሰዓት እላፊ ገደብ አምራች ኢንዱስትሪዎችን አይመለከትም'፦ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መም | YeneTube

"የተቀመጠው የሰዓት እላፊ ገደብ አምራች ኢንዱስትሪዎችን አይመለከትም"፦ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ

የተቀመጠው የሰዓት እላፊ ገደብ ለሁሉም አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደማይመለከት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ አስታወቀ።አሁን ባለው አገር የማዳን ግዳጅ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ይታወቃል፡፡

በዚህ ምክንያትም በአንዳንድ አካባቢዎች የሰዓት እላፊ ገደብ የተደረገ ቢሆንም በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ገደቡን ተግባራዊ ማድረግ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ጫና ስለሚያሳድርና ኢንዱስትሪዎችንም ወደ ኪሣራ ስለሚያስገባቸው የተቀመጠው የሰዓት እላፊ ገደብ ለሁሉም አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደማይመለከት ታውቆ፤ ኢንዱስትሪዎቹ አስፈላጊ የሆነ የራሳቸውን የጥበቃ ሥርዓት ከወትሮው በተለየ መልኩ አጠናክረው መደበኛ ሥራቸውን በተለመደው ሁኔታ እንዲቀጥሉ እንዲደረግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa