Get Mystery Box with random crypto!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ረቂቅ ሕገ መንግሥት የክልል መቀመጫን ሳይጠቅስ ማለፉ አወዛ | YeneTube

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ረቂቅ ሕገ መንግሥት የክልል መቀመጫን ሳይጠቅስ ማለፉ አወዛገበ!

መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. የተከናወነውን ሕዝበ ውሳኔ ተከትሎ በክልልነት ለመደራጀት የሚያስችለውን ድምፅ ያገኘው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ረቂቅ ሕገ መንግሥት፣ በተለያዩ ዞኖች ውይይት እየተደረገበት ቢሆንም፣ የክልል ከተማን በግልጽ ባለማስቀመጡ ውዝግብ እያስነሳ ነው፡፡

የክልሉ ረቂቅ ሕገ መንግሥት የክልል መቀመጫ አንድ ብቻ እንደማይሆንና በርካታ ከተሞች እንደሚኖሩ የሚደነግግና በስብሰባዎቹ የተገኙ ታዳሚዎች፣ የክልል ከተሞች በርካታ ቢሆኑም፣ የርዕሰ መስተዳድር መቀመጫ የሚሆነው የት ነው የሚለው ጥያቄ እያወዛገበ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ረቂቅ ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ ስድስት ላይ ርዕሰ ከተማን የሚመለከት ድንጋጌ የያዘ ሲሆን፣ ‹‹የክልሉ መንግሥት ከአንድ በላይ ከተሞች ይኖሩታል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፤›› ሲል ይደነግጋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa