Get Mystery Box with random crypto!

የፌደራሉ ዓቃቤ ሕግ ዛሬ በባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች ለመሠረተው የሽብር ክስ ዛ | YeneTube

የፌደራሉ ዓቃቤ ሕግ ዛሬ በባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች ለመሠረተው የሽብር ክስ ዛሬ በግልጽ ችሎት ምስክሮቹን ማሰማት መጀመሩን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። ዓቃቤ ሕግ ለዛሬ ከጠራቸው 9 ምስክሮች ዛሬ ችሎት ያቀረበው ሁለቱን ብቻ ነው። ከዘጠኙ ምስክሮች ሁለቱ የሚመሰክሩት በፓርቲው ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ ላይ እንደሆነ ዓቃቤ ሕግ ለችሎቱ አስረድቷል። ዓቀቤ ሕግ የቀሪዎቹን 12 ምስክሮቹን ስም ዝርዝር ዛሬ ለመገናኛ ብዙኀን በይፋ እንዲገልጽ ትናንት በችሎቱ ታዞ የነበረ ቢሆንም፣ ስም ዝርዝራቸውን ግን ዛሬ ሳይገልጽ ቀርቷል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa