Get Mystery Box with random crypto!

በቡራዩ ከተማ ከደለሳ ፒ ኤል ሲ የምንጣፍና ፕላስቲክ ፋብሪካ 2 ነብጥ 7 ሚሊየን ብር ግምት ያለው | YeneTube

በቡራዩ ከተማ ከደለሳ ፒ ኤል ሲ የምንጣፍና ፕላስቲክ ፋብሪካ 2 ነብጥ 7 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ንብረት በቡድን የዘረፉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
 
ግለሰቦቹ ገፈርሳ ቀበሌ ኖኖ ልዩ ቦታው ታጠቅ በተባለ ቦታ ከምሽቱ በግምት 3 ሰዓት ተኩል ላይ ዝርፊያ መፈጸማቸውን የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡የወረዳ 2 ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ሃላፊ ሳጅን ሙሉነህ ቀንኣ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ዘረፋው የተፈጸመው በዕለቱ ጥበቃ ላይ ከነበረው ግለሰብ ጋር በመመሳጠር እና ከተዘረፈ በኋላ እንደሚገዛቸው ከተስማማው ግለሰብ ጋር በጋራ በማቀድ ነው፡፡
 
ጥበቃው ወደ ፋብሪካው ቅጥር ግቢ ካስገባቸው በኋላ ውስጥ የነበሩ ግለሰቦችን በማፈን ዘረፋው መፈጸሙን የገለጹት ሳጅን ሙሉነህ ÷ ለዚህም ሁለት መኪናዎችን ተጠቅመዋል ነው ያሉት፡፡በዚህም 92 ካርቶንሲሲቲቪ ካሜራ፣ ቴሌቪዥን እና ሰነዶች መዘረፋቸውን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም በኤግዚቢትነት የተያዙትን ንብረቶች በቦታው ተገኝቶ ተመልክቷል፡፡
 
ፓሊስ ባደረገውም ክትትል ንብረቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ካኦጄጄ አካባቢ ወደ ሌላ መኪና ሲጫን እጅ ከፈንጅ መያዝ ተችሏል ነው ያሉት፡፡ከወንጀሉ ጋር ተያይዞም 11 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ያሉት ሳጅን ሙሉነህ ÷ እየተደጋገመ ለመጣው የቡድን ዘረፋ አስተማሪ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ብለዋል፡፡

Via Fana
@YeneTube @FikerAssefa