በአዲስ አበባ ከተማ የቋሚ ንብረት መሻሻጥን የሚከለክለው መመሪያ በቅርቡ ይነሳል ተባለ፡፡ Iltimos xabar YeneTube

Picture 1 from YeneTube 2021-10-20 13:22:02
በአዲስ አበባ ከተማ የቋሚ ንብረት መሻሻጥን የሚከለክለው መመሪያ በቅርቡ ይነሳል ተባለ፡፡

እንደ መኖሪያ ቤት ያሉ ቋሚ ንብረቶችን መሸጥና መግዛት ተከልክሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡በዚህም ምክንያት የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲም የስም ዝውውር እና ሥጦታን የተመለከቱ አገልግሎቶችን መስጠት ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ አቋርጦ ቆይቷል፡፡

አሁን ግን፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ መልኩ በመዋቀሩ እና የከተማዋ የመሬት ማኔጅመንትም አዲስ ኃላፊዎች ተሰይመውለት እንደገና በመደራጀቱ በዚህ ወር ውስጥ ከልካዩ መመሪያ ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል መባሉን ሸገር ሰምቷል፡፡

ሸገር ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ እንዳገኘው መረጃ ከኾነ፣ ምናልባትም እስከ ጥቅምት ወር መጨረሻ ቋሚ ንብረቶችን መሻሻጥና በሥጦታ የማስተላለፍ አገልግሎት ዳግም ይጀመራል፡፡

በመሆኑም ዜጎች ሕጋዊ ባለሆነው የመንደር ውል ቋሚ ንብረት ከመሸጥ እና ከመግዛት እንዲቆጠቡ እና አገልግሎቱ ዳግም እስኪጀመር በትዕግስት እንዲጠብቁ ኤጀንሲው አሳስቧል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
15.6K views