Get Mystery Box with random crypto!

መከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸው የአየር ድብደባዎች ኢላማቸውን የመቱ መሆናቸው ተገለጸ! የመከላከያ | YeneTube

መከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸው የአየር ድብደባዎች ኢላማቸውን የመቱ መሆናቸው ተገለጸ!

የመከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸው የአየር ድብደባዎች ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎች ላይ ብቻ እንደሆነና ኢላማቸውን የመቱ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
 
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች የመረጃ ማጣሪ ባወጣው መግለጫ፤ የመከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸውን የአየር ድብደባዎች በተመለከተ የተዛባ ግንዛቤ ቢኖርም፣ በተቃራኒው ጥቃቶቹ ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ ነው ብሏል።
 
የመከላከያ ሠራዊት የሚያከውናቸው እነዚህ ሥራዎች የሽብር ድርጅቱ ከባድ የጦር መሣሪያዎችን እና ሌሎች ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎችን ለመሸሸግ የሚጠቀምባቸውን እና ወደ ወታደራዊ መገልገያነት የቀየራቸውን የተወሰኑ ቦታዎች ከጥቅም ውጭ ለማድረግ ያለመ ነው ሲልም አስታውቋል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa