Get Mystery Box with random crypto!

ፌስቡክ የስያሜ ለዉጥ ሊያደርግ መሆኑ ተሰማ! ግዙፉ ማህበራዊ ሚዲያ ተቋም ፌስቡክ ከሚቀጥለዉ ሳ | YeneTube

ፌስቡክ የስያሜ ለዉጥ ሊያደርግ መሆኑ ተሰማ!

ግዙፉ ማህበራዊ ሚዲያ ተቋም ፌስቡክ ከሚቀጥለዉ ሳምንት ጀምሮ የስያሜ ለዉጥ ለማድረግ ማቀዱን ቨርጅ የተሰኘዉ የዜና ምንጭ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸዉ ሰዎች መስማቱን ጠቅሶ ዘግቧል።

አዲሱ ስያሜ በመጭዉ ማክሰኞ ጥቅምት 16፤ 2014 ዓ.ም በኩባንያው ዓመታዊ ኮንፈረንስ ላይ በድርጀቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ ይፋ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባዉ ያመላከተ ሲሆን ፌስቡክ በምላሹ በጉዳዩ ላይ አስተያየት አለመስጠቱም የተጠቀሰ ሲሆን የስያሜ ለውጥ ዜናው የተሰማው በኩባንያው የንግድ አሰራር ላይ ከአሜሪካ መንግስት የሚደረግበት ቁጥጥርና ወቀሳ እያየለ በመጣበት ወቅት መሆኑን ዘገባው አስታዉሷል።

በሲሊከን ቫሊ የቴክኖሎጂ መንደር ውስጥ የሚገኙ ኩባንያዎች አገልግሎታቸዉን በማስፋፋት በሚያደርጉት የንግድ ውድድር ስያሜያቸውን መቀየር ብዙም የተለመደ አይደለም።ከወራት በፊት ፌስቡክ የአገልግሎቱን ትኩረት ሜታቨርስ ወደተሰኘ ሰዎች የተለያዩ መሣሪያዎችን በመጠቀም በምናባዊ እውነታ (ቨርቹዋል ሪያሊቲ) ውስጥ ተሳትፎ የሚያደርጉበትን አሰራር ለማስተዋወቅ መዘጋጀቱን ይፋ አድርጎ ነበር።

Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa