Get Mystery Box with random crypto!

በሶማሌ ክልል የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለጸ! ከመሀል አገር በሶማሌ ክል | YeneTube

በሶማሌ ክልል የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለጸ!

ከመሀል አገር በሶማሌ ክልልን አቋርጦ ወደ ጎረቤት አገሮች የሚጓጓዝ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ባለፉት ሦስት ዓመታት ከደቡብ ክልልና ከመሀል አገር ተጭኖ ወደ ጎረቤት ኬንያ፣ ሶማሊያና ሌሎች መዳረሻ አገሮች ሊጓዝ ሲል በቁጥጥር ሥር የሚውለው የአደንዛዥ ዕፅ መጠን እየተበራከተ መምጣቱን የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ረዳት ኮሚሽነር መሐመድ አሊ አስታውቀዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አጠቃላይ የክልሉን የፀጥታ ጉዳይ አስመልክተው ማክሰኞ ጥቅምት 9 ቀን 2014 ዓ.ም. በጅግጅጋ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በየቀኑ በመኪና ተጭኖ ከአገር ሊወጣ ሲል የሚያዘው የዕፅ መጠን ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa