"YeneTube" Telegram Channel

Logo of telegram channel yenetube — YeneTube
655
Topics from channel:
Artland
Shegerhive
Ethiopia
Addisababa
Hiking
Logo of telegram channel yenetube — YeneTube
Topics from channel:
Artland
Shegerhive
Ethiopia
Addisababa
Hiking

"YeneTube" Telegram Channel

Channel address: @yenetube
Categories: Uncategorized
Subscribers: 168,725 (Update date: 2021-10-21)
Description from channel

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Comments

You must log in to post a comment.The latest Messages

2021-10-20 20:05:01 የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ረቂቅ ሕገ መንግሥት የክልል መቀመጫን ሳይጠቅስ ማለፉ አወዛገበ!

መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. የተከናወነውን ሕዝበ ውሳኔ ተከትሎ በክልልነት ለመደራጀት የሚያስችለውን ድምፅ ያገኘው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ረቂቅ ሕገ መንግሥት፣ በተለያዩ ዞኖች ውይይት እየተደረገበት ቢሆንም፣ የክልል ከተማን በግልጽ ባለማስቀመጡ ውዝግብ እያስነሳ ነው፡፡

የክልሉ ረቂቅ ሕገ መንግሥት የክልል መቀመጫ አንድ ብቻ እንደማይሆንና በርካታ ከተሞች እንደሚኖሩ የሚደነግግና በስብሰባዎቹ የተገኙ ታዳሚዎች፣ የክልል ከተሞች በርካታ ቢሆኑም፣ የርዕሰ መስተዳድር መቀመጫ የሚሆነው የት ነው የሚለው ጥያቄ እያወዛገበ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ረቂቅ ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ ስድስት ላይ ርዕሰ ከተማን የሚመለከት ድንጋጌ የያዘ ሲሆን፣ ‹‹የክልሉ መንግሥት ከአንድ በላይ ከተሞች ይኖሩታል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፤›› ሲል ይደነግጋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
9.6K views
Open / Comment
2021-10-20 19:39:43 የፌደራሉ ዓቃቤ ሕግ ዛሬ በባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች ለመሠረተው የሽብር ክስ ዛሬ በግልጽ ችሎት ምስክሮቹን ማሰማት መጀመሩን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። ዓቃቤ ሕግ ለዛሬ ከጠራቸው 9 ምስክሮች ዛሬ ችሎት ያቀረበው ሁለቱን ብቻ ነው። ከዘጠኙ ምስክሮች ሁለቱ የሚመሰክሩት በፓርቲው ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ ላይ እንደሆነ ዓቃቤ ሕግ ለችሎቱ አስረድቷል። ዓቀቤ ሕግ የቀሪዎቹን 12 ምስክሮቹን ስም ዝርዝር ዛሬ ለመገናኛ ብዙኀን በይፋ እንዲገልጽ ትናንት በችሎቱ ታዞ የነበረ ቢሆንም፣ ስም ዝርዝራቸውን ግን ዛሬ ሳይገልጽ ቀርቷል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
10.5K views
Open / Comment
2021-10-20 19:04:09 በቡራዩ ከተማ ከደለሳ ፒ ኤል ሲ የምንጣፍና ፕላስቲክ ፋብሪካ 2 ነብጥ 7 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ንብረት በቡድን የዘረፉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
 
ግለሰቦቹ ገፈርሳ ቀበሌ ኖኖ ልዩ ቦታው ታጠቅ በተባለ ቦታ ከምሽቱ በግምት 3 ሰዓት ተኩል ላይ ዝርፊያ መፈጸማቸውን የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡የወረዳ 2 ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ሃላፊ ሳጅን ሙሉነህ ቀንኣ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ዘረፋው የተፈጸመው በዕለቱ ጥበቃ ላይ ከነበረው ግለሰብ ጋር በመመሳጠር እና ከተዘረፈ በኋላ እንደሚገዛቸው ከተስማማው ግለሰብ ጋር በጋራ በማቀድ ነው፡፡
 
ጥበቃው ወደ ፋብሪካው ቅጥር ግቢ ካስገባቸው በኋላ ውስጥ የነበሩ ግለሰቦችን በማፈን ዘረፋው መፈጸሙን የገለጹት ሳጅን ሙሉነህ ÷ ለዚህም ሁለት መኪናዎችን ተጠቅመዋል ነው ያሉት፡፡በዚህም 92 ካርቶንሲሲቲቪ ካሜራ፣ ቴሌቪዥን እና ሰነዶች መዘረፋቸውን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም በኤግዚቢትነት የተያዙትን ንብረቶች በቦታው ተገኝቶ ተመልክቷል፡፡
 
ፓሊስ ባደረገውም ክትትል ንብረቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ካኦጄጄ አካባቢ ወደ ሌላ መኪና ሲጫን እጅ ከፈንጅ መያዝ ተችሏል ነው ያሉት፡፡ከወንጀሉ ጋር ተያይዞም 11 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ያሉት ሳጅን ሙሉነህ ÷ እየተደጋገመ ለመጣው የቡድን ዘረፋ አስተማሪ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ብለዋል፡፡

Via Fana
@YeneTube @FikerAssefa
11.4K views
Open / Comment
2021-10-20 13:22:02
Picture 1 from YeneTube 2021-10-20 13:22:02
በአዲስ አበባ ከተማ የቋሚ ንብረት መሻሻጥን የሚከለክለው መመሪያ በቅርቡ ይነሳል ተባለ፡፡

እንደ መኖሪያ ቤት ያሉ ቋሚ ንብረቶችን መሸጥና መግዛት ተከልክሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡በዚህም ምክንያት የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲም የስም ዝውውር እና ሥጦታን የተመለከቱ አገልግሎቶችን መስጠት ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ አቋርጦ ቆይቷል፡፡

አሁን ግን፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ መልኩ በመዋቀሩ እና የከተማዋ የመሬት ማኔጅመንትም አዲስ ኃላፊዎች ተሰይመውለት እንደገና በመደራጀቱ በዚህ ወር ውስጥ ከልካዩ መመሪያ ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል መባሉን ሸገር ሰምቷል፡፡

ሸገር ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ እንዳገኘው መረጃ ከኾነ፣ ምናልባትም እስከ ጥቅምት ወር መጨረሻ ቋሚ ንብረቶችን መሻሻጥና በሥጦታ የማስተላለፍ አገልግሎት ዳግም ይጀመራል፡፡

በመሆኑም ዜጎች ሕጋዊ ባለሆነው የመንደር ውል ቋሚ ንብረት ከመሸጥ እና ከመግዛት እንዲቆጠቡ እና አገልግሎቱ ዳግም እስኪጀመር በትዕግስት እንዲጠብቁ ኤጀንሲው አሳስቧል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
15.6K views
Open / Comment
2021-10-20 12:47:43
Picture 1 from YeneTube 2021-10-20 12:47:43
መከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸው የአየር ድብደባዎች ኢላማቸውን የመቱ መሆናቸው ተገለጸ!

የመከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸው የአየር ድብደባዎች ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎች ላይ ብቻ እንደሆነና ኢላማቸውን የመቱ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
 
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች የመረጃ ማጣሪ ባወጣው መግለጫ፤ የመከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸውን የአየር ድብደባዎች በተመለከተ የተዛባ ግንዛቤ ቢኖርም፣ በተቃራኒው ጥቃቶቹ ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ ነው ብሏል።
 
የመከላከያ ሠራዊት የሚያከውናቸው እነዚህ ሥራዎች የሽብር ድርጅቱ ከባድ የጦር መሣሪያዎችን እና ሌሎች ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎችን ለመሸሸግ የሚጠቀምባቸውን እና ወደ ወታደራዊ መገልገያነት የቀየራቸውን የተወሰኑ ቦታዎች ከጥቅም ውጭ ለማድረግ ያለመ ነው ሲልም አስታውቋል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
14.4K viewsedited  
Open / Comment
2021-10-20 11:26:02
Picture 1 from YeneTube 2021-10-20 11:26:02
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ ጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ ለፓርቲዎች እና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ይፋ አደርገ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን በአብዛኛው የአገራችን ክፍሎች አከናውኖ እጠናቋል።በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በሚገኙ 17 ምርጫ ክልሎች (በአብዛኛው የክልል ምክር ቤት) ምርጫ ሳይካሄድ ቀርቷል።በክልል የሚያስፈልገው የጸጥታ ፍላጎቶች ከተሟሉ ምርጫው ሊከናወንበት የሚችልበትን ጊዜያዊ ሰሌዳ ለፓርቲዎች እና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ይፋ አድርጓል።

@YeneTube @FikerAssefa
14.2K views
Open / Comment
2021-10-20 11:09:34
Picture 1 from YeneTube 2021-10-20 11:09:34
ፌስቡክ የስያሜ ለዉጥ ሊያደርግ መሆኑ ተሰማ!

ግዙፉ ማህበራዊ ሚዲያ ተቋም ፌስቡክ ከሚቀጥለዉ ሳምንት ጀምሮ የስያሜ ለዉጥ ለማድረግ ማቀዱን ቨርጅ የተሰኘዉ የዜና ምንጭ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸዉ ሰዎች መስማቱን ጠቅሶ ዘግቧል።

አዲሱ ስያሜ በመጭዉ ማክሰኞ ጥቅምት 16፤ 2014 ዓ.ም በኩባንያው ዓመታዊ ኮንፈረንስ ላይ በድርጀቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ ይፋ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባዉ ያመላከተ ሲሆን ፌስቡክ በምላሹ በጉዳዩ ላይ አስተያየት አለመስጠቱም የተጠቀሰ ሲሆን የስያሜ ለውጥ ዜናው የተሰማው በኩባንያው የንግድ አሰራር ላይ ከአሜሪካ መንግስት የሚደረግበት ቁጥጥርና ወቀሳ እያየለ በመጣበት ወቅት መሆኑን ዘገባው አስታዉሷል።

በሲሊከን ቫሊ የቴክኖሎጂ መንደር ውስጥ የሚገኙ ኩባንያዎች አገልግሎታቸዉን በማስፋፋት በሚያደርጉት የንግድ ውድድር ስያሜያቸውን መቀየር ብዙም የተለመደ አይደለም።ከወራት በፊት ፌስቡክ የአገልግሎቱን ትኩረት ሜታቨርስ ወደተሰኘ ሰዎች የተለያዩ መሣሪያዎችን በመጠቀም በምናባዊ እውነታ (ቨርቹዋል ሪያሊቲ) ውስጥ ተሳትፎ የሚያደርጉበትን አሰራር ለማስተዋወቅ መዘጋጀቱን ይፋ አድርጎ ነበር።

✍Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
13.6K views
Open / Comment
2021-10-20 09:40:17
Picture 1 from YeneTube 2021-10-20 09:40:17
ሞሮኮ 310 ህገወጥ ስደተኞች ባህር ሊያቋርጡ ሲሉ መያዟን ገለጸች!

የሞሮኮ የባህር ኃይል 310 የሚሆኑ ህገወጥ ስደተኞች በሜድትራኒያንና በአትላንቲክ ባህር ዳርቻዎች አድርገው ወደ አውሮፓ ሊያቀኑ ሲሉ መያዙን አስታውቋል፡፡አብዛኞቹ ስደተኞች ከሰሀራ በታች የመጡ የመጡ ሲሆን ከስደተኖቹ ውስጥ 23 ሴቶችና 9 ህጻናት ይገኙበታል፡፡ስደተኞቹ በሚንቀሳቀሱበት ጉዜ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ማለፋቸውን የሞሮኮ መንግስት አስታውቋል፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
13.2K views
Open / Comment
2021-10-20 09:28:02
Picture 1 from YeneTube 2021-10-20 09:28:02
በሶማሌ ክልል የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለጸ!

ከመሀል አገር በሶማሌ ክልልን አቋርጦ ወደ ጎረቤት አገሮች የሚጓጓዝ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ባለፉት ሦስት ዓመታት ከደቡብ ክልልና ከመሀል አገር ተጭኖ ወደ ጎረቤት ኬንያ፣ ሶማሊያና ሌሎች መዳረሻ አገሮች ሊጓዝ ሲል በቁጥጥር ሥር የሚውለው የአደንዛዥ ዕፅ መጠን እየተበራከተ መምጣቱን የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ረዳት ኮሚሽነር መሐመድ አሊ አስታውቀዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አጠቃላይ የክልሉን የፀጥታ ጉዳይ አስመልክተው ማክሰኞ ጥቅምት 9 ቀን 2014 ዓ.ም. በጅግጅጋ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በየቀኑ በመኪና ተጭኖ ከአገር ሊወጣ ሲል የሚያዘው የዕፅ መጠን ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
12.7K views
Open / Comment