Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵ

Logo of telegram channel ethyoop — ኢትዮጵ
Logo of telegram channel ethyoop — ኢትዮጵ
Channel address: @ethyoop
Categories: Blogs
Language: Not set
Country: Ethiopia
Subscribers: 2.56K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


The latest Messages

2020-09-25 20:23:44 #የገንዘብ_ታሪክ_በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ገንዘብ አስቀርጸው መገበያየትን የጀመሩት የአክሱም ነገሥታት መሆናቸውን ታሪክ ያስረዳናል። በላይ ግደይ በ1983 ዓ.ም. ታትሞ በወጣውና ገንዘብ ባንክና መድኀን በኢትዮጵያ በተሰኘ መጽሀፋቸው ላይ በግልጽ እንዳሰፈሩት ከጥንት አክሱማዊያን ነገሥታት መካከል ንጉሥ ኢንደቢስና ንጉሥ አፊላስ የራሳቸውን ህጋዊ ገንዘብ አሳትመው በውጭና በውስጥ በገንዘብ አማካኝነት ይገበያዩ ነበር። ይህም የአክሱማዊያን ስልጣኔ በዘመኑ ምን ደረጃ ላይ ደርሶ እንደነበር ከሚመሰክሩ ጉዳዮች አንደኛው ነው። አክሱም በጊዜው ከነበሩ አራት ታላላቅ ሥልጣኔዎች መካከል አንዷ እንደነበረች ባዕዳን ሳይቀር የመሰከሩት ሀቅ ነው። በዚህም ከፋርስ እስከ ቻይና ከአረቢያ እስከ ሮም የተዘረጋ የውጭ ግንኙነትን አክሱማዊያን መመስረት ችለው ነበር።
ከንጉስ ኢንደቢስና ከንጉሥ አፊላስ ውጪ ብዙ አክሱማዊያን ነገሥታት ገንዘብ አሳትመው እንደነበር ቢታወቅም በዚህ ረገድ ስሙ ጎልቶ የሚነሳውና የሐበሻ ቆስጠንጢኖስ እየተባለ የሚጠራው ገናናው ንጉሥ ኢዛና ነው። የንጉሥ ኢንደቢስና የንጉስ አፊላስ ገንዘቦች በአንደኛው ገጽ የራሳቸው ምስል በገብስና በስንዴ ዛላ ተከበው በሌላው ገጽ ደግሞ የጸሀይና የጨረቃ ምስልና አንዳንዴም አጭር ምሳሌያዊ ንግግር ተቀርጸውባቸው ይገኛሉ። እነኚህ ሳንቲሞች በጥቂቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ይገኙ እንጂ አብዛኛዎቹ በውጪው ዓለም ተበትነዋል። በተለይም በኤደን (የመን) ብዙ የአክሱማዊያን ገንዘቦች ይገኛሉ። በላይ ግደይ በመጽሀፋቸው የዚህን ምክንያት ሲያስቀምጡ አክሱማዊያን በጊዜው የምንንም ይገዙ ስለነበር ለወታደር ደሞዝ ሊከፈል የሄደ ገንዘብ ሳይሆን አይቀርም ይላሉ። የንጉሥ ኢዛናን ገንዘብ ስንመለከት ሁለት አይነት ገንዘቦችን እናገኛለን። ንጉሡ ክርስትናን ከመቀበሉ በፊት ያሳተመው ገንዘብ የነበረው ሲሆን ክርስትናን ከተቀበለ በኋላ ደግሞ የመስቀል ምልክትን ያካተተ ገንዘብ አሳትሟል። በዚህም በዓለም የመስቀል ምልክትን በገንዘቡ ላይ ያሳተመ ቀደምት ንጉሥ ለመሆን በቅቷል።
የአክሱማዊያን ስልጣኔ ከጠፋ በኋላ ኢትዮጵያ ዓለምን ረስታ ዓለምም ኢትዮጵያን ረስቶ ዘመናት አልፈዋል። በዚህ መካከል ኢትዮጵያ ገንዘብ አሳትማ ከመገበያየት ስልጣኔ ወርዳ እቃን በእቃ በመለወጥ የግብይት ሂደት ውስጥ ረዥም ዘመናትን ካሳለፈች በኋላ በመካከሉ ማሪያ ትሬዛ ታለር የተባለው የመገበያያ ገንዘብ በጎረቤት ሀገሮች በኩል በነጋዴዎች አማካይነት ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ዋና የመገበያያ ገንዘብ ሊሆን ቻለ። ይህ ገንዘብ እ.አ.አ. በ1751 ዓ.ም ለኦስትሪያዋ ንግሥት መታሰቢያ የወጣ ገንዘብ ነበር። ይህ ታላቅ ተወዳጅነትን ያተረፈው ገንዘብ በአዋጅ በኢትዮጵያ ገንዘብ እስከተተካበት 1937 ዓ.ም. ድረስ በስፋት ለረዥም ጊዜ ሲያገለግል ቆይቷል።

አጼ ምንሊክ እና አጼ ኃ/ሥላሴ ያወጡት ገንዘብ

አጼ ምንሊክ በዘመናቸው ስላሳተሙት ገንዘብ ባላምባራስ መኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል በዝክረ ነገር መጽሀፋቸው ይህን ብለዋል።

"ከ፲ ፱ ፻ ፩(1901) ፡ ዓ ፡ ም ፡ በፊት ፡ ምንም ፡ ቀደም ፡ ብሎ ፡ በነምሳዋ ፡ ንግ ሥት ፡ በማሪ፡ ቴሬዝ ፡ መልክ ፡ የታተመ ፡ የብር ፡ ገንዘብ ፡ በኢትዮጵያ ፡ ቢታወቅ ፤ አብዛኛው ፡ ሕዝብ ፡ ይሻሻጥና ፡ ይገዛዛ ፡ የነበረው ፡ በጥ ይትና ፡ ባሞሌ ፥ ሸቀጥ ፡ በመለዋወጥ ፡ ነበር ፤ ኋላ ፡ ግን ፡ ዐፄ ፡ ምኒልክ ፡ ባንድ ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ መንግሥት ፡ የሚኖር ፡ ሕዝብ ፡ በየጐጡ፡ እንደ ፡ ፈቀደውና ፡ እንደ ፡ ወደደው ፡ መተዳደር ፡ የያዘው ፤ መንግ ሥት ፡ አስቦ ፡ ተፈላጊ ፡ የሆነውን ፡ ባያደራጅለት ፡ ነው ፡ ብለው ፡ ለመ ላው ፡ ሕዝባቸው ፡ አንድነትን ፡ ሰጥቶ ፡ ያስተዳደሩንም ፡ ሥራ ፡ ምቹ ፡ ለማድረግ ፡ በመልካቸውና ፡ በስማቸው ፡ ገንዘብ ፡ አሳትመው ፡ በዚሁም ፡ ሕዝቡ ፡ እንዲገበያይበት ፡ ባ፲ ፱ ፻ ፩(1901) ፡ ዓ ፡ ም ፡ ቀጥሎ ፡ ያለውን ፡ ዐዋጅ ፡ ኣደረጉ ።
በኢትዮጵያ ፡ የመገበያያ ፡ ገንዘብ ፡ ብር ፡ እንዲሆን ፡ የተነገረ ፡
ዐዋጅ ።
ሞአ ፡ አንበሳ ፡ ዘእምነገደ ፡ ይሁዳ ። ምኒልክ ፡ ሥዩመ ፡ እግዚአብሔር ፡
ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ዘኢትዮጵያ ። ከዚህ ፡ ቀደም ፡ ነጋዴም ፥ ወታደርም ፡ ባላገርም ፡ የሆንክ ፡ ሰው ፡ ሁለ ፡ በየገበያውና ፡ በየመንገዱ ፡ በስፍራውም ፡ ሁሉ ፡ በጥይት ፡ ስት ገበያይ ፡ ትኖር ፡ ነበር ፤ አሁን ፡ ግን ፡ በኔ ፡ መልክና ፡ ስም ፡ የተሠራ ፡ ብር ፣ አላድ ፣ ሩብ ፣ ትሙን ፤ መሓለቅ ፡ ኣድርጌልኻለሁና ፡ በዚህ ፡ ተገ በያይ ፡ እንጂ ፡ እንግዴህ ፡ በጥይት ፡ መገበያየት ፡ ይቅር ፡ ብያለሁ ፡ የሚሸጥም ፡ ጥይት ፡ ከቤቱ ፡ ያለው ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ እጅምሩክ ፡ እየወሰደ ፡ ለጅምሩክ ፡ ሹም ፡ ይስጥ ፣ ጥይትም ፡ ለመግዛት ፡ የፈለገው ፡ ሰው ፡ እጅ ምሩክ ፡ እየሄደ ፡ ይግዛው ፤ ይኸንንም ፡ ዐዋጅ ፡ አፍርሶ ፡ ጥይት ፡ ርስ ፡ በራሱ ፡ ሲሻሻጥና ፡ ሲገዛዛ ፡ የተገኘ ፡ ሰው ፤ ገዥውም ፡ ሻጭውም ፡ ስለ ቅጣታቸው ፡ ባ፩(1) ፡ ጥይት ፡ ፩ ፡ ፩ ፡ ብር ፡ ይክፈሉ ፤ ይህነንም ፡ ዐዋጅ ፡ አፍርሶ ፡ ጥይት ፡ ሲሻሻጥ ፡ አግኝቶ ፡ ወደ ፡ ዳኛ ፡ ያመጣ ፡ ሰው ፡ በቅ ጣት ፡ ከሚከፍሉት ፡ ገንዘብ ፡ እኩሌታውን ፡ ሊያዥው ፡ መርቄለታለሁ።
(ኅዳር ፡ ፳ ፪ (22) ፡ ቀን ፡ ፲ ፱ ፻ ፩ (1901) ፡ ዓ፡ ም ፡ እንጦጦ ፡ ከተማ ፡ ተጻፈ ።)
አዲሱ ፡ ገንዘብ ፡ የተሠራው ፡ ከብር ፡ ስለ ፡ ሆነ ፤ በራሱ ፡ ዋጋ ፡ ያ ለው ፡ በመሆኑ፡ ጭምር ፡ በመላው ፡ ግዛታቸው ፡ በፍጥነት ፡ ያለችግር ፡ ታወቀ ። አንድ፡ ብር፡ ሁለት ፡ አላድ ፡ አራት ፡ ሩብ ፡ ስምንት ፡ ትሙን ፡ ዐሥራ ፡ ስድስት ፡ መሐለቅ ፡ ይመነዘራል ።ይኸም፡ ለማንኛቸውም፡ ጕዳይ ፡ በገበያ ፡ ላይ ፡ ለመገበያየት ፡ የተ መቸ ፡ በመሆኑና ፡ ቢያስቀምጡት ፡ ስለማይበላሽ ፥ በሕዝቡ ፡ ዘንድ ፡ በጣም፡ የተወደደና ፡ የተፈለገ ፡ ሆነ ።
ከዚያም ፡ ወዲህ ፡ በን ፡ ነ ፡ ዘውዲቱ ፡ ዘመን ፡ ለመንግሥትም ፡ ለድኻም ፡ የተመቸ ፡ እንዲሆን ፡ በማሰብ ፡ ቤሳ ፡ የተባለ ፡ ከመዳብ ፡ የተ ሠራ ፡ የብር ፡ ፴ ፪ኛ(32ኛ) ፡ ባፄ ፡ ምኒልክ ፡ መልክ ፡ ታተመ ። ቀጥሎም፣ በባንክ ፡ በኩል ፡ በሁለት፣ ባምስት ፤ባሥር፤ ባምሳ፣ባንድ፡ መቶ፤ ባምስ መቶና ፡ ባንድ ፡ ሺሕ፡ ብር ፡ ሒሳብ ፡ የታተመ ፡ ባንክ ፡ ኖት ፡ የተባለ - የገንዘብ ፡ ወረቀት፡ ወጣ ።
ግርማዊ ፡ ቀዳማዊ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ የንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ዘውድ ፡ በጫኑ ፡ ዘመን ፡ ባ፲ ፱ ፻ ፳ ፫(1923) ፡ ዓ ፡ ም ፡ ግን ፡ በጣም ፡ ተሻሽሎ ፡ እንደ ፡ ዓለም ፡ ሕግ ፡ ሁሉ ፡ በሳንቲም ፡ የሚታሰቡ ፡
መቶ ፡ ሳንቲም ፡(አንድ ፡ ብር) ፡
አምሳ ፡ ሳንቲም ፡(አላድ)
ካያ፡አምስት፡ ሳንቲም ፡ (ሩብ)
ዐሥር ፡ ሳንቲም
አምስት ፡ ሳንቲም
አንድ ፡ሳንቲም ኒኬል፡ የሆኑ ፡ ገንዘቦች ፡ በግርማዊነታቸው፡መልክና፡ ስም፡ታትመው ፡ ጠላት፡በኢትዮጵያ፡እገባ፡ ድረስ፡ እስካ፱ ፻ ፳ ፰ ፡ ዓ ፡ ም ፡ ሕዝቡ፡ በደስታ፡ ተቀብሎ ፡ ሲገበያይባቸው : ቈይቷል ።"

ይቀጥላል
4.9K views17:23
Open / Comment
2020-09-25 12:13:27
#የገንዘብ_ታሪክ_በኢትዮጵያ

:
:
:
:
:
:
°
°
°
#ዛሬ_ማታ
3.3K views09:13
Open / Comment
2020-09-08 19:00:58 #ኢትዮጵ
ኢትዮጵያ በራሷ ቀመር ጊዜን የምትቆጥር አገር ናት። በዚህም መሰረት ከአስራ ሁለቱ ባለሰላሳ ቀናት ወራት በተጨማሪ አስራ ሶስተኛ ወርም አላት። ለዚህም ነው የአስራ ሶስት ወር ጸጋ ሀገር መባሏ። ይህች ወር ጷጉሜን ትባላለች። ይህቺ የዘመን ድልድይ የሆነች ወር አምስት፣ ሲሻት ስድስት፣ አልፎም ሰባት ቀናት የምትሆንበት ጊዜ አለ። ለመሆኑ ጳጉሜን ከዬት መጣች? ጥንተ መሰረቷስ ምንድነው? ለዚህ ጥያቄ መልስ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የዳንኤል ክብረት እይታዎች በሚለው ጦማሩ ላይ “ጳጉሜን - አምስት፣ ስድስት፣ ሰባት” በሚል ርዕስ ያሰፈረው ጽሁፍ ይህን ይላል።
“ጳጉሜ ማለት በግሪክ ‹ጭማሪ› ማለት ሲሆን ዓመቱን በሠላሳ ቀናት ስንከፍለው የሚተርፉትን ዕለታት ሰብስበው የሰየሟት ተጨማሪ ወር ናት፡፡ ወይም በየዕለቱ በፀሐይና በጨረቃ አቆጣጠር መካከል የሚፈጠረውን ልዩነት ሰብስበው ያከማቹባት ወር ትባላለች፡፡ ዓመቱ በዐውደ ፀሐይ ሲለካ 365 ቀናት ከ15 ኬክሮስ 6 ካልዒት ሲሆን በጨረቃ ሲለካ ደግሞ 354 ቀናት ከ22 ኬክሮስ፣ 1 ካልዒት፣ 36 ሣልሲት፣ 52 ራብዒት፣ 48 ኀምሲት ነው፡፡ (60 ኬክሮስ አንድ ቀን ነው)በሁለቱ መካከል(በፀሐይና በጨረቃ) በዓመት ውስጥ ያለው ልዩነት 11 ቀናት ከ7 ኬክሮስ ይሆናል፡፡ [በነገራችን ላይ በዘመን አቆጣጠራችን ውስጥ ከዕለት በታች የምንቆጥርባቸው ስድስት መለኪያዎች አሉ፡፡ ኬክሮስ፣ ካልዒት፣ ሣልሲት፣ ራብዒት፣ ኀምሲትና ሳድሲት፡፡ 60 ሳድሲት አንድ ኀምሲት፣ 60 ኀምሲት አንድ ራብዒት፣ 60 ራብዒት አንድ ሣልሲት፣ 60 ሳልሲት አንድ ካልዒት፣ 60 ካልዒት ደግሞ 1 ኬክሮስ ይሆናል፡፡ 60 ኬክሮስ ደግሞ 1 ዕለት፡፡ 1 ኬክሮስ 24 ደቂቃ ነው]
ጳጉሜን ለማግኘት የሚጠቅመን የየዕለቱን ልዩነታቸውን መመልከቱ ነው፡፡ በየዕለቱ በጨረቃና በፀሐይ መካከል 1 ኬክሮስ 52 ካልዒት(60 ካልዒት አንድ ኬክሮስ ነው)፣ ከ 31 ሣልሲት(60 ሣልሲት አንድ ካልዒት ነው) ይሆናል፡፡[ይህም ማለት 5 ሰዓት ከ48 ደቂቃ ከ46 ካልዒት(ሴኮንድ?)] ይህ ልዩነት በአንድ ወር ምን እንደሚደርስ ለማወቅ በ30 እናባዛው፡፡ 30 ኬክሮስ፣ 1560 ካልዒት፣ ከ930 ሣልሲት ይሆናል፡፡ የዓመቱን ለማግኘት ደግሞ በ12 እናባዛው፡፡ 360 ኬክሮስ(፩)፣ 18720 ካልዒት(፪)፣ 11160 ሣልሲት(፫) ይመጣል፡፡
ቀደም ብለን 60 ኬክሮስ አንድ ዕለት ይሆናል ባልነው መሠረት 360 ኬክሮስ ለ60 ሲካፈል 6 ዕለታትን ይሰጠናል(፩)፡፡ 18720 ካልዒትን(፪) በስድሳ በማካፈል 312 ኬክሮስን እናገኛለን፡፡ ያም ማለት ትርፉን 12 ኬክሮስ ትተን 300ውን ኬክሮስ ለ60 በማካፈል 5 ዕለት እናገኛለን፡፡ ይኼም ማለት 5 ዕለት ከ12 ኬክሮስ(፬) ይሆናል፡፡ 11160 ሣልሲትን(፫)ለ60 ብናካፍለው 186 ካልዒት ወይም ደግሞ 3 ኬክሮስና 6 ካልዒት(፭) ይሆናል ማለት ነው፡፡
ከላይ ኬክሮስን በዓመቱ ቀናት አባዝተን ያገኘነው(፩) 6 ዕለት አለ፡፡ ይኼ ዕለት ሕጸጽ ይባላል፡፡ ፀሐይና ጨረቃን እኩል መስከረም አንድ ላይ ዓመቱን ብናስጀምራቸው ፀሐይ የወሯ መጠን ምንጊዜም ሠላሳ ሲሆን ጨረቃ ግን በአንደኛው ወር 29 በሌላኛው ወር ግን 30 ስለምትሆን ዓመቱ እኩል አያልቅም የጨረቃ ዓመት ነሐሴ 24 ቀን ያልቃል፡፡ ይህም ማለት ጨረቃ በሁለት ወር አንድ ጉድለት ታመጣለች፡፡ ያንን ነው ሊቃውንቱ ሕጸጽ(ጉድለት) ያሉት፡፡ በዚህም መሠረት ከላይ ኬክሮሱን(፩) በዓመቱ ቀናት አባዝተን ያገኘነውን 6 ዕለት ለጨረቃ ሕጸጽ ስንሰጠው የመስከረም/ ጥቅምት (1)፣ የጥቅምት/ ኅዳር(2)፣ የጥር/ የካቲት(3)፣ የመጋቢት/ ሚያዝያ(4)፣ የግንቦት/ ሰኔ (5)፣ የሐምሌ ነሐሴ (6) ሆነው ተካፍለው ያልቃሉ፡፡
በሌላም በኩል ደግሞ በጨረቃና በፀሐይ ዑደት መካከል በዓመት ያለው ልዩነት 11 ቀናት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት) ይሆናል፡፡ ስድስቱን ዕለታት ጨረቃ ለምታጎልበት (ሕጸጽ) ብንሰጠው ቀሪ 5 ዕለት ይኖረናል፡፡ ጳጉሜ ማለት እነዚህ 5 ቀናት ናቸው፡፡ አሁን የአሥራ አንዱን ዕለታት ከፈጸምን ሽርፍራፊዎቹን (15 ኬክሮስና 6 ካልዒት) እንይ፡፡
ከላይ እንዳየነው በፀሐይና ጨረቃ ዓመታት መካከል የተፈጠሩትን 11 ቀናት ስድስቱ ለሕጸጽ ማሟያ ሲገቡ የቀሩት 5 ዕለታት ናቸው ጳጉሜ የምትባለውን ወር በመሠረታዊነት የፈጠሯት፡፡ በጎርጎርዮሳውያኑ አቆጣጠር እነዚህ 5 ተጨማሪ ዕለታት በጃንዋሪ፣ ማርች፣ ሜይ፣ ጁላይና ኦገስት ላይ ስለተጨመሩ እነዚህ ወራት 31 ለመሆን ተገድደዋል፡፡ (ይህንን የከፈለው በ46 ቅልክ የነበረው ዩልየስ ቄሣር ነው፡፡ ለአራቱ ወሮች 30 ቀን፣ ለአንዱ 28/29 (በየአራት ዓመቱ)፣ ለቀሩት ሰባት ወሮች ደግሞ 31 ሰጥቷቸዋል፤ ለአምስቱ ወሮች 31 ያደረጋቸው ከጳጉሜ ወስዶ ሲሆን ለሁለቱ ወሮች አንዳንድ ቀን የጨመረላቸው ከፌቡርዋሪ 2 ቀናት ወስዶና ወሩን 28 አድርጎ ነው)፡፡
ከእንግዲህ የሚቀሩን ከላይ የየዕለቱን ልዩነት ለዓመት ስናባዛ (ቁጥር ፪ና ፫ ተመልከት) የቀሩን 15 ኬክሮስና 6 ካልዒት ናቸው፡፡ ሁለቱን ከላይ ያየናቸውን (፬ና፭) ስንደምራቸው (12 ኬክሮስ + 3 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት) 15 ኬክሮስ ከ 6 ካልዒት ይመጣሉ፡፡
ቀደም ብለን አንድ ዕለት 60 ኬክሮስ ነው ብለናል፡፡ ስለዚህም አንድ ዕለት (60 ኬክሮስ) ለማግኘት ከላይ ያገኘነውን 15 ኬክሮስ በ 4 ማባዛት አለብን፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ጳጉሜ 6 የምትሆነው እነዚህ በየዓመቱ የተጠራቀሙት 15 ኬክሮሶች አንድ ላይ መጥተው በአራት ዓመት አንድ ጊዜ አንድ ዕለት ስለሚሆኑ ነው፡፡ እርሷም ሠግር(leap year) ትባላለች፡፡ ጎርጎርዮሳውያኑ ይህቺን ሠግር በፌቡርዋሪ ወር ላይ ጨምረው ወሩን በየአራት ዓመቱ አንድ ጊዜ 29 ቀን ያደርጉታል፡፡
15ቱ ኬክሮስ በአራት ዓመት ተደምረው አንድ ዕለት መጡና በአራት ዓመት አንዴ ጳጉሜን ስድስት አደረጓት፡፡ የቀረችው 6 ካልዒትስ (ቁጥር ፭) የት ትግባ?
ካልዒት አንዲት ዕለት ትሆን ዘንድ 3600 ካልዒት ያስፈልጋሉ፡፡ ይህንን ያህል ካልዒት ለማግኘት 600 ዓመታት ያስፈልጉናል፡፡ ለዚህ ነው ጳጉሜ በየስድስት መቶ ዓመታት ሰባት የምትሆነው፡፡ እስካን የጠየቅኳቸው የባሕረ ሐሳብና የታሪክ ሊቃውንት በታሪካችን ውስጥ ጳጉሜን 7 የሆነችበትን ዘመን እንደማያውቁ ነግረውኛል፡፡ ሒሳቡ ሲሰላ በየ 600 ዓመቱ ሰባት ትሆናለች ቢባልም አስቦ በስድስት መቶኛው ዓመት ሰባት የሚያደርጋት እንደሌለ ይናገራሉ፡፡ በፈረንጆቹ ብሂል ‹ፌብሩዋሪ 30› ማለት የመሆን ዕድል ያለው ነገር ግን ሆኖሞ የማያውቅ ሊሆንም የማይችል(possible but never happen)› ተደርጎ እንደተወሰደው ሁሉ ምናልባት በኛም ጳጉሜን 7 ማለት እንደዚያው ይሆን ይሆናል፡፡
4.6K views16:00
Open / Comment
2020-09-04 20:00:48 ​የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አጠቃላይ መረጃ

የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሁለት ዞኖችንና ስምንት ወረዳዎችን አካቷል፡፡

የስፍራው አቀማመጥ
ክልሉ በኢትዩጵያ ምእራባዊ ጫፍ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን፣ በምእራብ ደቡብና ሰሜን ሱዳንን ሲያዋስን፣ በደቡብና በምስራቅ ደግሞ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትን ያዋስናል፣ እንዲሁም የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜንና ምስራቅ ያዋስኑታል፡፡
ርእሰ ከተማ
የክልሉ ርእሰ ከተማ ጋምቤላ ነው፡፡

የቆዳ ስፋት
ክልሉን በቅርቡ የተቀላቀለውን ወረዳ ሳይጨምር የክልሉ የቆዳ ስፋት 25‚274 ኪ.ሜ ይደርሳል፡፡

ስነ-ህዝብ
በ1987 በተደረገው የህዝብ ቆጠራ መስረት፣ የህዝብ ብዛቷ 182.862 ሲሆን ከነዚህ ውስጥም 92‚090 የሚሆነው ወንዶች ሲሆን 88‚960 ደግሞ ሴቶች ናቸው፡፡
153‚438 /84.9%/ የሚሆነው ህዝብ በክልሉ በገጠራማ ቦታዎች ውስጥ የኖራል፡፡
ዋና ዋናዎቹ የክልሉ ብሄረሰቦች ኑዌር፣ አኙዋክ፣ መዘንገር፣ አፓና እና ኮሞ ይባላሉ፡፡ በተጨማሪም የኦሮሞ፣ አማራ፣ ከምባታ፣ ከፉ፣ ትግሬ እና ሌሎችም ብሄረሰቦች በክልሉ ይኖራሉ፡፡
ከጠቅላላው የህዘብ ስብጥር 46 ከመቶ ኑዌር፣ 27 ከመቶ አኙዋክ፣ 8 ከመቶ አማራ 6 ከመቶ ኦሮሞ፣ 5.8 ከመቶ መዠንገር፣ 4.1 ከመቶ ከፋ ፣ 2 ከመቶ ሞካ ፣ 1.6 ከመቶ ትግሬ እና 5.5 ከመቶ የሚሆነው ደግሞ ከደቡብ ህዝቦች ናቸው፡፡

አማርኛ የክልሉ የስራ ቋንቋ ነው፡፡
የተለያዩ እምነት ተከታዬች የሚኖሩበት ክልል ነው፡፡ 44 ከመቶ የኘሮቴስታንት፣ 24.1 ከመቶ የኦርቶዶክስ፣ 10.3 ከመቶ የባህላዊ ሀይማኖት ፣ 5.1 ከመቶ የእስልምና፣ 3.2 ከመቶ የካቶሊክ እና 12.7 ከመቶ የሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች ይኖሩበታል፡፡

ዋነኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች
አብዛኛው የክልሉ ህዝብ አርብቶ አደር ነው፡፡ በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ሰሊጥና ሌሎች የቅባት ክህሎችን፣ ማንጐ፣ ሙዝና ወዘተ በማምረት ይተዳደራሉ፡፡
የመሬት አቀማመጥ እና የአየር ንብረት
ክልሉ በአብዛኛው ጠፍጣፋ የመሬት አቀማመጥ ሲኖረው፣ እርጥበት ያለው ሞቃት የአየር ንብረትን ይዟል፡፡
ለ17 አመት የተመዘገበው አመታዊ የአየር ንብረቱ 615.9 ሚ.ሜ ሲሆን፣ 21.12ocዝቅተኛ እና 35.9ocከፍተኛ የሙቀት መጠን በአማካኝ ተመዝግቦል፡፡

ወንዞችና ሀይቆች
ባሮ የተባለው፣ በኢትዮጵያ ሙስጥ ብቸኛው ለመጓጓዣ የሚያገለግለው ወንዝም በዚሁ ክልል ነው የሚገኘው፡፡ ወንዙ ክልሉን ከሱዳን ጋር ያገናኛል፡፡

ቱሪዝምና ቅርሶች
የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ በክልሉ የሚገኝ የቱሪስት መሰህብ ነው፡፡ በተጨማሪም እንደ ዝሆን፣ ጐሽ፣ ዝንጀሮና በቀቀን የመሳሰሉ የዱር እንሰሳት ይገኙበታል፡፡
3.6K views17:00
Open / Comment
2020-09-02 20:00:28
3.0K views17:00
Open / Comment
2020-09-02 20:00:27 ኢትዮጵ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አጠቃላይ መረጃ


የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በ10 አሰተዳደራዊ ዞኖች፣ በአንድ ልዩ ዞን፣ በ105 ወረዳዎች እና በ78 የከተማ ማዕከሎች የተዋቀረ ነው፡፡ አማርኛ የክልሉ የስራ ቋንቋ ነው፡፡

የስፍራው አቀማመጥ
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜናዊ-ምዕራብ እና በመሀከለኛው ሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኝ ሲሆን ክልሉ በሰሜን ከትግራይ ክልል፣ በምስራቅ ከአፋር ክልል፣ በደቡብ ከኦሮሚያ ክልል፣ በደቡብ-ምዕራብ ከቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልል እንዲሁም በደቡብ ከሱዳን ሪፐብሊክ ጋር ይዋሰናል፡፡

የቆዳ ስፋት
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 170‚752 ስኩ.ኪ.ሜ የሚገመት የቆዳ ስፋት ይሸፍናል፡፡

ርእሰ ከተማ
ባህር ዳር የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ ከተማ ነች፡፡

ስነ-ህዝብ
በ1994 በተገኘው የህዝብ ቆጠራ መሰረት የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የህዝብ ብዛት 13,834,297 ሲሆን ከዚህም ውስጥ 6,947,546 ወንዶች እና 6,886,751 ሴቶች ናቸው፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ 1‚265‚315 በከተሞች ኗሪ ሲሆን 12‚568‚982 በገጠራማው የክልሉ ቦታዎች ይኖራል ይህም ከአጠቃላዩ የህዝብ መጠን 90 ከመቶ የሸፍናል፡፡
በሀይማኖት ረገድም 81.5% የኦርቶዶክስ ክርስትያን፣ 18.1% የእስልምና እና 014% የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነው፡፡
በብሄር ስብጥር አኳያም 91.2% የአማራ፣ 3% የኦሮሞ፣ 2.7% የአገው/አዊ፣ 1.2% የቅማንት እና 1% የአገው/ካምይር ብሄረሰቦች ይኖራሉ፡፡

ዋነኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትከሚገኘው ህዝብ 85% የሚሆነው በግብርና ስራ ላይ የተሰማራ ነው፡፡ ክልሉ የጤፍ ምርትን በዋነኛነት ከሚያመርቱ ክልሎች አንዱ ነው፣ ከዚህም በተጨማሪ ገብስ፣ ስንዴ፣ የቅባት እህሎች፣ ማሽላ፣ ለውዝ፣ ሽንብራና ባቄላ በከፍተኛ ደረጃ የሚመረቱ ሰብሎች ናቸው፡፡
እንደ ጥጥ፣ ሰሊጥ፣ ሱፍ እና የሸንኮራ አገዳ የመሳሰሉት የአገዳ ሰብሎችም በሰፊውና በድንግሉ የክልሉ ቆላማ ለም መሬት ላይ ይመረታሉ፡፡
ከጣና ሀይቅና አባይ ወንዝን ከመሳሰሉ ትላልቅ ተፋሰሶች የሚገኘው የውሀ ሀብት ለክልሉ የመስኖ እርሻ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡
ከክልሉ የመሬት ሀብት 450‚000 ሄክታር የሚሆነው ለእርሻና ለመስኖ ስራ በተለይም ለፍራፍሬና ለአበባ ምርት የተመቸ ነው፡፡
የመሬት አቀማመጥ እና የአየር ንብረት
የአማራ ክልል ከመሬት አቀማመጥ አንፃር ሲታይ በሁለት ዋናዋና ክፍሎች ይመደባል እነሱም የከፍተኛ ተራራማ አካባቢዎች እና የዝቅተኛ ቦታዎች ናቸው፡፡
የከፍተኛ ቦታዎቹ ከባህር ጠለል በላይ ከ1‚500 ሜትር በላይ ሲገኙ የክልሉን ሰሜናዊ እና ምስራቃዊ ቦታዎች ይሸፍናሉ፡፡ እነዚህ ከፍተኛ ቦታዎች በሰንሰላታማ ተራራዎች የተከበቡ ናቸው፡፡
በ4620 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኘው የራስ ደጀን ተራራ ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ የተራራ ከፍታ ሲሆን፤ 4620 ሜትር ከፍታ ያለው የጉና ተራራ፣ 4184 ሜትር ከፍታ ያለው የጮቄ ተራራ እና 4190 ሜትር ከፍታ ያለው የአቡነ ዮሴፍ ተራራ በዚሁ የክልሉ አካባቢዎች የሚገኙ ናቸው፡፡
የዝቅተኛው የክልሉ ክፍል በዋነኛነት የምዕራባዊውንና የምስራቁን አካባቢ የሚሸፍን ሲሆን፤ ከ500 እስከ 1‚500 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ከፍታ አለው፡፡
በክልሉ የተለያዩ የአየር ንብረት ያላችው አካባቢዎች ሲገኙ 31% ቆላማ፣ 44% ወይና ደጋማ፣ 25% ደጋማ ቦታዎች ናቸው፡፡
በአብዛኛው የክልሉ ቦታዎች አመታዊ አማካኝ የሙቀት መጠን ከ15 c አስከ 21 c ይደርሳል፡፡
ክልሉ በሀገሪቱ እስከ 80% የሚደርሰውን የዝናብ መጠን ያስመዘግባል፡፡ ከፍተኛው የዝናብ መጠን በክረምት ወራት የሚመዘገበው ሲሆን፤ ይህም ወራት ከሰኔ አጋማሽ እስከ መስከረም መጀመሪያ ይዘልቃል፡፡

ወንዞችና ሀይቆች
የአማራ ብሄራዊ ክልል በ3 የወንዝ ተፋሰሶች የተከፈለ ነው እነሱም አባይ፣ ተከዜ እና አዋሽ ወንዞች ናቸው፡፡
ጥቁር አባይ ከሁሉም ረጅሙ ሲሆን 172‚254 ስኩዌር ኪ.ሜ የቆዳ ስፋት ይሸፍናል፡፡ ይሄው ወንዝ ካርቱም ከሚገኘው ነጭ አባይ ጋር እስኪገናኝ ድረስ ያለው ርዝመት 1‚450 ኪ.ሜትር ነው፡፡ ከዚህም ውስጥ 800 ኪ.ሜትሩ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያደርገው ጉዞ ነው፡፡
የአባይ ወንዝ
የተከዜ ወንዝ ወደ 88‚000 ስኩዌር ኪ.ሜትር የቆዳ ስፋት ይሸፍናል፡፡
ከነዚህ ወንዞች በተጨማሪ አንገረብ፣ ሚሌ፣ ከሰም እና ጀማ የተባሉ ወንዞች በክልሉ የሚገኙ ተፋሰሶች ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ በስፋቱ አንደኛ የሆነው የጣና ሀይቅ በዚሁ ክልል ይገኛል፡፡ ይህ ሀይቅ 3‚600 ስኩዌር ኪ.ሜትር ስፋት አለው፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን ሌሎች በእሳተ ጎመራ አማካኝነት የተፈጠሩ እንደ ዘንገና፣ ጉደና፣ አርዲቦ እና ሎግያ የተባሉ አነስተኛ ሀይቆችም በክልሉ ይገኛሉ፡፡
በክልሉ የሚገኙት ሀይቆችና ወንዞች ለሀይድሮ ኤለክትሪክ ሀይል ማመነጪያነት፣ ለመስኖ አገልግሎት እና ለአሳ ማጥመድ የሚሆን እምቅ ቸሎታ ያላቸው ናቸው፡፡

የቁም ከብት ሀብት
በክልሉ ወደ 9.1 ሚሊዮን የቀንድ ከብቶች፣ 8.4 ሚሊዮን በጎችና ፍየሎች፣ 1.6 ሚሊዮንየጋማ ከብቶች እንዲሁም 8.5 ሚሊዮን ዶሮዎች ይገኛሉ፡፡ ይህም ማለት በሀገሪቱ ከሚገኘው የቁም ከብት 40 ከመቶው በዚህ ክልለ የሚገኝ ነው፡፡ ይህ ትልቅ የቁም ከብት ሀብት ክልሉን ለስጋና ወተት ምርት፣ ለቆዳና ሌጦ ምርት ምቹ ያደርገዋል፡፡

የዱር እንስሳት
በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የሚገኙት እንደ ዋልያ አይቤክስ፣ የሰሜን ቀይ ቀበሮ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ እና ሌሎች ብርቅዬ እንስሳት በክልሉ የገኛሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ የተለያዩ የአእዋፍ አይነቶች ይኖራሉ፡፡

ማዕድን
በአማራ ክልል ውስጥ እንደ ከሰል/ኮል፣ ሼል፣ ላይምስቶን፣ ሊግናይት፣ የኖራ ድንጋይ፣ ሲሊካ፣ ድኝ እና ቤንቶኔት የተባሉ ማእድናት ይገኛሉ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ የፍልውሀ ምንጮችና የማእድን ውሀዎች በክልሉ የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች ናቸው፡፡

ቱሪዝም እና ቅርሶች
በ12ኛው ክፍለ ዘመን የተፈለፈለው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት፣ የጎንደር ጥንታዊ ቤተመንግስቶች እና ሌሎችም ታሪካዊ መስህቦች በክልሉ ይገኛሉ፡፡
በጣና ሀይቅ ደሴቶች ላይ በሚገኙ ገዳማት ጥንታዊ የግድግዳ ላይ ስእሎች፣ ተጠብቀው የቆዩ የጥንት ነገስታት አፅሞችና ቅሪተ አካሎች እንዲሁም ልዩ ልዩ የእደ-ጥበብ ውጤቶች ይገኛሉ፡፡
ገዳማትን ከያዙት የጣና ሃይቅ ደሴቶች አንዱ የሆነው ፣ ደቅ ደሴት
የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘውን ብርቅዬ እንስሳ ዋልያ አይቤክስን ለመጎብኘት እንዲሁም የተራራ መውጣት ስፖርት ለማካሄድ ከፍተኛ ቁጠር ያለው ቱሪስት የሚሄድበት የቱሪስት መዳረሻ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ለአለም አቀፍ ቅርስ ጥበቃ ካስመዘገበቻቸው 8 ቅርሶች ሶስቱ የሚገኙት በዚሁ ክልል ነው፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ቅርሶች ባሻግር የጢስ አባይ ፏፏቴ፣ በሰሜን ሸዋ የሚገኙት ልዩ አፈጣጠር ያላቸው ዋሻዎችና አለቶች አንዲሁም የ"መርጡለ ማርያም" ቤተክርስትያን ሌሎች የቱሪስት መስህቦች ናቸው፡፡
3.2K views17:00
Open / Comment
2020-09-01 20:09:43 ​​​ኢትዮጵ
የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አጠቃላይ መረጃ

የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በ4 አሰተዳደራዊ ዞኖች ፣ በአንድ ልዩ ዞን ፣ በ35 ወረዳዎች እና በ74 ከተማዎች የተዋቀረ ነው። የክልሉ ምክር ቤት የከፍተኛ አስተዳደር አካል ሲሆን 152 የካቢኔ አባላትን የያዘ ነው። የህግ አስፈፃሚው አካል በ16 ተወካዮች የተዋቀረ ነው።
የስፍራው አቀማመጥ
የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜናዊው የኢትዮጵያ ጫፍ የሚገኝ ሲሆን ክልሉ በሰሜን ከኤርትራ፣ በምስራቅ ከአፋር ክልል፣ በደቡብ ከአማራ ክልል እንዲሁም በምእራብ ከሱዳን ሪፐብሊክ ጋር ይዋሰናል፡፡


ርእሰ ከተማ
መቀሌ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ ከተማ ነች፡፡
የቆዳ ስፋት
የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት 80000 ስኩ.ኪ.ሜ የሚገመት የቆዳ ስፋት ይሸፍናል፡፡

ስነ-ህዝብ
በ1994 በተገኘው የህዝብ ቆጠራ መሰረት የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የህዝብ ብዛት 3,136,267 ሲሆን ከዚህም ውስጥ 1,542,165 ወንዶች እና 2,667,789 ሴቶች ናቸው።
በሀይማኖት ረገድም 95.5% የኦርቶዶክስ ክርስትያን፣ 4.19% የእስልምና እና 0.4% የካቶሊክ እምነት ተከታይ ነው።
በብሄር ስብጥር ረገድም 94.98% የትግራዊ፣ 2.6% የአማራ፣ 0.7% የኢሮብ እና 0.05% የኩናማ ብሄረሰቦች ይኖራሉ፡፡ ትግርኛ የክልሉ የስራ ቋንቋ በመሆን ያገለግላል።

ዋነኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች
በትግራይ ብሔራዊ ክልል ከሚገኘው ህዝብ 83% የሚሆነው በግብርና ስራ ላይ የተሰማራ ነው፡፡
ጤፍ፣ ስንዴ እና ገብስ ዋነኛ የሰብል ምርቶች ሲሆኑ ባቄላ፤ የጥራጥሬ እህሎች፣ ሽንኩርት እና ድንች እንዲሁ በክልሉ ይመረታሉ፡፡
ተዳፋታማ የመሬት አቀማመጥ ባላቸው የክልሉ አካባቢዎች የመስኖ እና የእርከን መፍትሄዎችን በመጠቀም የእርሻ ስራ ይከናወንባቸዋል፡፡
የትግራይ ክልል የጥጥ፣ የእጣን፣ የሰሊጥ እና የተለያዩ ማእድናትን ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በማቅረብ ይታወቃል፡፡
ከክልሉም የመሬት ይዞታ 1.5 ሚሊዮን ሄክታር መልማት የሚችል ሲሆን ከዚህም ውስጥ 1 ሚሊዮን ሄክታሩ ለእርሻ አገልገሎት የዋለ ነው፤ የተቀረው 420,877 ሄክታር መሬት ደግሞ የእርከን ስራን በመጠቀም የለማ ነው፡፡
የተለያዩ የእደ-ጥበብ(እንደ ወርቅ ማንጠር፣ የስዕል እና የእንጨት ቅርፃ ቅርፅ) ስራዎች ሌላው በክልሉ በሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎች ላይ የሚስተዋሉ የስራ አንቅስቃሴዎች ናቸው፡፡

የመሬት አቀማመጥ እና የአየር ንብረት
ምንም እንኳን ክልሉ ከ3,250 - 3,500 ሜትር ከፍታ ባላቸው የተራራ ሰንሰለቶች እና የተፈጥሮ መስህቦች የተከበበ ቢሆንም፤ ለዘመናት ሲፈራረቅበት የቆየ የመሬት መሸርሸር፣ የደን መጨፍጨፍ እና ከመጠን በላይ የሆነ የግጦሽ መሬት አጠቃቀም የክልሉን መሬት ለደረቅና ዛፍ-አልባ ሜዳዎች፣ኮረብታዎችና ተራራዎች አጋልጦታል፡፡
ይህ ክልል እጅግ በጣም የተለያዩ የከፍታ ልዩነቶችን ያስተናግዳል፡፡
የክልሉ የከፍታ መጠን ከባህር ጠለል በላይ ከ600 - 2,700 ሜትር ሲሆን
የተከዜ ሸለቆ ከባህር ጠለል በላይ 550 ሜትር ከፍታ ላይ ሲገኝ
"የክሳድ ጉዶ" የተራራ ጫፍ ደግሞ ከባህር ጠለል በላይ በ3,935 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም በመሀከላዊ ደጋማ አካባቢዎች ከሚገኙ የትግራይ ውብ የተፈጥሮ እይታዎች አንዱ ያደርገዋል፡፡
በክልሉ የተለያዩ የአየር ንብረት ያላችው አካባቢዎች ሲገኙ 39% ቆላማ፣ 49% ወይና ደጋማ፣ 12% ደጋማ ቦታዎች ናቸው፡፡ የክልሉ አመታዊ አማካኝ የዝናብ መጠን ከ450 – 980 ሚ.ሜ ይደርሳል፡፡

ወንዞችና ሀይቆች
ከአማራ ብሄራዊ ክልል የሚነሳው የተከዜ ወንዝ እንዲሁም ከኤርትራ የሚነሳው የመረብ ወንዝ የትግራይ ክልልን የሚያቋርጡ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ናቸው፡፡
እንደ ገባ፣ ወሪ፣ በርበር፣ አርቋ እና ጠጠር የተባሉ ለመስኖ ስራ ጠቃሚ የሆኑ አነስተኛ ወንዞችም በክልሉ ይፈሳሉ፡፡
የተከዜ ወንዝ የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫነት እያገለገለ ይገኛል፡፡
የተከዜ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኀይል ማመንጫ ግድብ
ሌላው በክልሉ የሚገኘው የአሸንጌ ሀይቅ ውብ የሆኑ አእዋፋትን ለመመልከት እና አሳ ለማጥመድ የተመቸ እና ቀልብን የሚስብ የተፈጥሮ መስዕብ ነው፡፡
ውብ አእዋፋት በአሸንጌ ሃይቅ

የቁም ከብት ሀብት
በክልሉ ወደ 11.51 ሚሊዮን የሚጠጋ የቤት እንስሳት ሲገኙ ከነዚህም ውስጥ 2.15 ሚሊዮን የቀንድ ከብቶች፣ 5.63 ሚሊዮን በጎችና ፍየሎች እንዲሁም 392,000 የጋማ ከብቶች ናቸው፡፡

የዱር እንስሳት
ዝሆን፣ ነብር፣ አጋዘንና የምኒሊክ ድኩላ በክልሉ የሚገኙ የዱር አራዊቶች ናቸው፡፡

ማዕድን
የትግራይ ክልል በኢትዮጵያ ውስጥ በማዕድን ሀብት ከበለፀጉ አካባቢዎች አንዱ ነው፡፡
በክልሉ ከተገኙ የብረት ማዕድናት ውስጥ ወርቅ፣ መዳብ፣ የብረት ኦር, ዚንክ, ሊድ እና ኒኬል ይገኙበታል፡፡
አስቤስቶስ, የሲሊከን አሸዋ, ካኦሊን, ግራፋይት, ላይም ስቶን, እብነ-በረድ, ግራናይት እና ዶሎማይት የተባሉ ብረት ያልሆኑ ማዕድናት በክልሉ ይገኛሉ፡፡

ቱሪዝም እና ቅርሶች
የትግራይ ክልል በተደጋጋሚ ከሚጠቀሱ የሰው ልጅ የስልጣኔ እና የባህል ዝርዝሮች ውስጥ የሚገኝ እና በአለም ላይ ከሚታወቁ ጥቂት ታሪካዊ ቦታዎች አንዱ ነው፡፡
ክልሉ በአህጉራችን ከሚገኙ እጅግ በጣም ወሳኝ የሆኑ የታሪክ ሀውልቶች የሚገኙበት ነው፡፡ ይህም ማለት ከቅድመ - ክርስትና በፊት የቆሙ ታላላቅ ሀውልቶች ይገኙበታል፡፡
ከክርሰቶስ ልደት በፊት በ2ኛው ክፍለ ዘመን የቆመው የአክሱም ሀውልት፣
ከክርሰቶስ ልደት በፊት በ5ኛው ክፍለ ዘመን እና ከቅድመ አክሱም ግዛት በፊት የተገነባው "የጨረቃ ቤተ-መቅደስ"፣
የንግስት ሳባ የመታጠቢያ ቤት እና ቤተ-መንግስት፣ የታቦተ ፅዮን ማደሪያ ይህ ሁሉ በክልሉ የሚገኙ ዋናዋና ቅርሶች ናቸው፡፡
የአክሱም ሃውልት
ታቦተ ጽዮንም ከእየሩሳሌም ቤተ-መቅደስ የመጣ እንደሆነ ይታመናል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ክልሉ በአለም ላይ ታላቅ የሆኑትን ሁለት ሀይማኖቶች እነሱም ክርስትናን በ4ኛው እንዲሁም እስልምናን በ6ኛው ክፍለ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት እንደ በር አገልግሏል፡፡
የነጃሺ መሰጊድም በክልሉ የሚገኝ ሌላው የታሪክ እና የሀይማኖት መስህብ ነው፡፡

በክልሉ ከ120 በላይ የሚሆኑ ለገዳም አገልግሎት የሚውሉ ፍልፍል አብያተ ክርስትያናት እና ዋሻዎች ሲገኙ በትግራይ በሚገኙ ተራራዎች ሁሉ ተሰራጭተው ይገኛሉ፡፡
እነዚሁ ገዳማትና ዋሻዎች በውስጣቸው የተለያዩ የብር መስቀሎችን፣ የሚያንፀባርቁ ዘውዶችን፣ ጥንታዊ የብራና ፅሁፎችን እና የሳባ ፊደላት የተቀረጸባቸውን ድንጋዮች ይዘዋል፡፡ እነዚህና ሌሎች መሰል የባህል ቅርሶች ተደማምረው ክልሉን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተመን የለሽ አካባቢ ያደርገዋል፡፡
3.1K views17:09
Open / Comment
2020-08-07 19:00:37
ውድ የኢትዮጵ ተከታታዮች ስለ ኢትዮጵያ አጠቃላይ መረጃ የጀመርነውን ጽሑፍ እንደወደዳችሁት ተስፋ አለን። በቀጣይ ደግሞ ሁሉንም ክልሎች ለመዳሰስ እንሞክራለን። ኢትዮጵያን ሙሉ አድርገን እንመለከት ዘንድ እንደሚረዳን ተስፋ አለን።

ኢትዮጵያ ሐገራችንና እና እኛ ኢትዮጵያውያን ታሪካችን እንደመልካችን ሁሉ ዥንጉርጉር ነው። ለአንዱ አያታችን የተመቸች ኢትዮጵያ ለአንዱ አያታችን ጎርባጣ ነበረች። አንዱን ያስተማረ፥ ለወግ ለማዕረግ ያበቃ ስርዓት ሌላውን በጥይት ቆልቷል፥ ከሀገር ባለቤትነት አግልሏል። ይህ ግን ማናቸውም የብዙ ዘመን ታሪክ ያለው አገር እና አበረው የኖሩ ህዝቦች ሊኖራቸው ከሚችል የተለየ እውነታ አይመስለኝም። ምናልባት እንዲህ ያለው የትርክት ብዝሃነት ዛሬ ላይ ለእኛ ታላቅ አደጋ የጋረጥብን ሁሉንም ትርክቶች እኩል የእኛው ታሪክ እንደሆኑ አለማመቻመች መቀበል ስላቃተን ይሆን? የአንዱ ጀግኖች ለሌላው ባይሆኑም አብረን ለቆምንባት አገር ያደረጉትን በጎም ሆነ ክፉ በግልፅ መወያየት መቻል አለብን። የእኔንም እንዲሁ። የእኔን አትንኩ የእናንተን አርክሱ አይነት ውይይት ግን ምናልባት ተጨማሪ ቁርሾ ይፈጥር እንደሆነ እንጂ ትርፍ አይኖረውም።"
መልእክታችን ነው።

እናመሠግናለን!!
ኢትዮጵ
5.2K views16:00
Open / Comment
2020-08-06 20:10:55 ኢትዮጵ
•የኢትዮጵያ አጠቃላይ መረጃ

ጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ ነሃሴ 14፣ 2004 ዓም ከዚህ አለምበሞት ሲለዩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር የነበሩት ኃይለማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው ተሾሙ።

•የመንግስት አወቃቀር

ኢትዮጵያ የፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት አወቃቀር ሲኖራት በ10 የብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት እንዲሁም በሁለት የከተማ መስተዳድሮች የተዋቀረች ነች፡፡ አወቃቀራቸውም በሕገ መንግስቱ በተደነገገው መሰረት «በህዝብ አሰፋፈር ፣ ቋንቋ ፣ ማንነት እና ፈቃድ ላይ» ተመስርቶ ሲሆን ክልሎቹም የሚከተሉት ናቸው።

1. የትግራይ ክልል
2. የአፋር ክልል
3. የአማራ ክልል
4. የኦሮሚያ ክልል
5. የሶማሌ ክልል
6. የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
7. የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል
8. የጋምቤላ ክልል
9. የሀረሪ ክልል
10. የሲዳማ ክልል
11. በተጨማሪም የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ መስተዳደሮች ይገኙበታል።

እነዚህ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት አንዲሁም ሁለቱ የከተማ መስተዳደሮች በ800 ወረዳዎቸና ወደ 15000 በሚጠጉ ቀበሌዎች(5000 የከተማና 10000 የገጠር) የተከፋፈሉ ናቸው።

•ህዝብ
በ1999 ዓ.ም በተደረገው የህዝብና ቤት ቆጠራ እና ትንበያ መሰረትም በአሁኑ ጊዜወደ 90 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ አላት፡፡ ከዚህም ውስጥ ወደ 84 ከመቶ የሚጠጋው በገጠሪቱ የኢትዮጵያ ክፍል ሲኖር የተቀረው በከተማና ከፊል ከተማ በሆኑ ቦታዎች ይኖራል፡፡

ኢትዮጵያ ከ80 በላይ የሚሆኑ ብሄር ብሄረሰቦች የሚገኙባት ሀገር ነች። የኦሮሞ፣ የአማራ፣ እና የትግራይ እንዲሁም የሶማሌ ብሄረሰቦች ከጠቅላላው የአገሪቱዋ ሕዝብ ቁጥር ክ3/4ኛ በላይ የሚሆነውን ይይዛሉ።
በሃይማኖት በኩልም ክርስትናና እስልምና በስፋት የሚስተዋልባት አገር ናት። እስልምና ከ 25-30% ፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታዮች ከ 60-65% ፡ ፐሮቴስታንት ደግሞ 10% የሚሆነውን ድርሻ ይሸፍናል።
የወንድ አማካኝ እድሜ 53.42 ዓመት ሲሆን የሴት ደግሞ 55.42 ዓመት ነው።
የዕድሜ ስብጥር (በመቶኛ)
0-14 አመት - 42.8%
15-19 አመት - 10.5%
20-49 አመት - 37.4%
50-59 አመት - 4.9%
60ና ከዛ በላይ: 4.4%

•ቋንቋዎች

በኢትዮጵያ ውስጥ ከ80 በላይ ብሄር ብሄረሰቦች የሚኖሩ ሲሆን በቋንቋም በኩል ከ80 በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎች የሚነገርባት ሀገር ናት፡፡
በአሁኑ ወቅት በእብዛኛው ኢትዮጵያውያን የሚነገሩት ቋንቋዎች አማርኛ እና ኦሮምኛ ሲሆኑ፤ አማርኛ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ነዋሪዎች የመማሪያ፤ የመገበያያ እንዲሁም የስራ ቋንቋ ሆኖ የቆየ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የብሄራዊ ቋንቋ ነው።
በኢትዮጵያ የሚነገሩት ቋንቋዎች ወደ አራት ዋና ዋና የቋንቋ ክፍሎች ሊካተቱ ይችላሉ። እነዚሁም:-

#ኩሻዊ: ወደ 19 ቋንቋዎችን የያዘ
#የአባይ-ሰሃራዊ: ወደ 20 ቋንቋዎችን የያዘ
#ኦሞአዊ: ወደ 23 ቋንቋዎችን የያዘና
#ሴማዊ: ወደ 12 ቋንቋዎችን የያዙ ናቸው።

ኩሻዊ ከሚባሉት ቋንቋዎች ዋና ዋናዎቹ ኦሮምኛ፣ ሶማልኛ፣ አፋርኛ፣ ሲዳምኛ፣ ሃዲያኛ እና ከምባትኛ ሲሆኑ ከአባይ-ሰሃራዊ የቋንቋ ምድብ የሚካተቱት በርታኛ፣ ኩናማኛ፣ ጉሙዝኛ፣ ሙርሲኛ እና የመሳሰሉት ናቸው። እንደ ወላይትኛ፣ ጋሞኛ፣ ከፋኛ፣ ሃመርኛ የመሳሰሉት የኦሞአዊ ቋንቋ ዘሮች ሲሆኑ አማርኛ፣ ትግርኛ፣ ጉራጊኛ፣ ስልጢኛ፣ ሀደሪኛ እና መሰል ቋንቋዎች ከሴማዊ ቋንቋዎች ይመደባሉ።
የሴሚቲክ ምንጭ ያላቸው እንደ አማርኛ ያሉት ቋንቋዎች የራሱ የሆነ የተለየ የፊደል ስርአት ያላቸው ሲሆን ይህም ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ብቸኛዋ ባለ ጥንት ፊደል ሀገር ያደርጋታል። እነኚህ የሴሚቲክ ምንጭ ያላችው ቋንቋዎች ግዕዝ የተባለ በአሁኑ ወቅት ከቤተክርስትያን ውጭ ለእለት ተእለት ግልጋሎት ላይ የማይውል ግንድ ዘር አላቸው።

•ኢኮኖሚ

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዋነኛነት በግብርና ዘርፍ የተያዘ ነው ከዚህም ከሀገሪቱ ጠቅላላ የውስጥ ምርት 45 ከመቶውን ይሸፍናል፣ 10 ከመቶ የሚሆነው የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሲሆን፣ 13.3 ከመቶው ደግሞ የማምረቻው ዘርፍ ይይዛል፡፡
የወጪ ንግድም የሚከናወን ሲሆን ከዚህም ውስጥ እስከ 60 ከመቶ የሚደርሰው የቡና መላክ ወጪ ንግድ ነው፡፡

•ግብርና

እርሻ የአገሪቱ የጀርባ አጥንት ሲሆን አገሪቱ ከዚሁ የኢኮኖሚ ዘርፍ ቡና፣ የቅባት እህሎች፣ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ስኳር እና የከብት መኖ ወደ ውጭ ትልካለች፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የከብት ሀብት ልማት በመኖሩ ከዚህ ዘርፍ የቁም ከብት፣ ቆዳና ሌጦ በመላክ የውጭ ምንዛሬ ታገኛለች፡፡
ኢትዮጵያ ካሏት አጠቃላይ ዘርፎች ውስጥ የግብርና ዘርፍ ቀዳሚውን ሲይዝ በ2006/07 ዓ.ም በተገኘ አመታዊ ስሌት መሰረት ግብርና 45.9 ከመቶ የሚሆነውን የሀገሪቱ የምርት ውጤት ይሸፍናል፡፡ ወደ 45 ከመቶ የሚሆነው የሀገሪቱ መሬት ለግብርና ስራ ምቹ ነው፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ወደ 10‚556 ሄክታር መሬት ብቻ ለእርሻ አገልግሎት የዋለ ነው፡፡

•የአምራች ዘርፍ

በ2006/07 ዓ.ም 13.3 ከመቶ የሚሆነውን የሀገሪቱን ጠቅላላ ምርት ያስመዘገበው ይህ ዘርፍ ነው፡፡ ከዚህም ዘርፍ የምግብ፣ የለስላሳ መጠጦች፣ የጨርቃ ጨርቅና የቆዳና ሌጦ ውጤቶች ይገኙበታል፡፡
ዘርፉ በዋነኛነት ከግብርና የሚገኙ ምርቶችን ለማቀነባበር እና ለማምረት ይንቀሳቀሳል፡፡ በዚህም ለሀገር ውስጥ ገበያ የሚውሉ የሸማቾች እቃዎችን ያቀርባል፡፡ ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶችም ጨርቃ ጨርቅ፣ የታሸገና የቀዘቀዘ ስጋ፣ በከፊል የተጨረሱ ቆዳና ሌጦ፣ ስኳርና ሞላሰስ፣ የእግር አልባሳት፣ ትንባሆ፣ ለስላሳ መጠጦች፣ ዘይት፣ ሰም ፣ ሌዘርና የሌዘር ውጤቶችን ያቀርባል፡፡

•አገልግሎት ሰጪ ዘርፍ
የአገልግሎት ሰጪ ዘርፍ 40.5 ከመቶ የሚሆነውን የሀገር ውስጥ ምርት ይሸፍናል፡፡ ይህ ዘርፍ በአሁኑ ወቅት ቀስ በቀስ በማደግ ላይ የሚገኝ ሲሆን በ1996/97 ዓ.ም ከነበረበት 36 ከመቶ በ2006/07 40.8 ከመቶ ሊደርስ ችሏል፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው በተፈጠረው የትምህርት፣ የሪል-እስቴት፣ የኪራይ እና የንግድ እንቅስቃሴዎች፣ በጅምላና ችርቻሮ ንግድ፣ እንዲሁም የሆቴልና ሬስቶራንት ንኡስ-ዘርፎች እድገት ምክንያት ነው፡፡

•የመገበያያ ገንዘብ:

የኢትዮጵያ የገንዘብ መለኪያ ብር ነው
1 ብር ከ100 ሳንቲሞች ጋር እኩል ነው
የብር ኖቶች
ባለ 1 ብር ኖት
ባለ 5 ብር ኖት
ባለ 10 ብር ኖት
ባለ 50 ብር ኖት
ባለ 100 ብር ኖት
የመዳብ ሳንቲሞች፡ 1፣5፣10፣25፣ እና 50 ሳንቲሞች
የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት በአየር መንገዶች እና ፈቃድ ባለቸው ሆቴሎች ይገኛል፡፡

ምንጭ
የኢትዮጵያ መንግስት ፖርታል
ማእከላዊ ስታትስቲክስ እጀንሲ
የኢትዮጵያ ብሄራው ባንክ ድረ-ገፅ
4.2K views17:10
Open / Comment
2020-08-05 19:00:08 ኢትዮጵ
የኢትዮጵያ አጠቃላይ መረጃ

•መልክዓምድር
ኢትዮጵያ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ከ3-14 ዲግሪ ሰሜን እና ከ33-48 ዲግሪ ምሥራቅ የምትገኝ አገር ስትሆን የቆዳ ስፋቱዋም 1,127,127 ካሬ ኪ.ሜ. ነው።
በሰሜን ከኤርትራ፣ በምዕራብ ከሱዳን፣ በደቡብ ከኬኒያ፣ እንዲሁም በምሥራቅ ከጅቡቲ እና ከሶማሊያ ጋር ትዋሰናለች።

የኢትዮጵያ አብዛኛው ግዛት በተራሮችና በሀይቆች የተሞላ ሲሆን፣ ታላቁ የምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ እነዚህኑ ከፍተኛ ቦታዎች ከሰሜን ምሥራቅ ወደ ደቡብ ምዕራብ በመጋደም ለሁለት ይከፍላቸዋል። በስምጥ ሸለቆው ዙሪያም በረሃማ የሆኑ ዝቅተኛ ቦታዎች ይገኛሉ። ይኅን መሰሉ የመልክዓ-ምድር ልዩነት አገሪቷ የተለያዩ የአየር ንብረት፣ የአፈር፣ የዕፅዋት እና የሕዝብ አሰፋፈር ገጽታዎች እንዲኖራት አስችሏታል።
(ምስል 1•የኢትዮጵያ ካርታ 2•የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ)

በከፍታና በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የተነሣ በኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት ዐይነት የአየር-ንብረት ክልሎች ይገኛሉ።
እነሱም:-
➊ደጋ - ከፍታቸው ከባሕር ጠለል 2400 ሜትር የሚጀምር እና የሙቀት መጠናቸው ከ 16 ዲግረ ሴ.ግ የማይበልጥ፤
➋ወይናደጋ - ከፍታቸው ከባሕር ጠለል ከ1500 እስከ 2400 ሜትር፣ ሙቀታቸውም ከ16 ዲግረ ሴ.ግ እስከ 30 ዲግረ ሴ.ግ የሚደርስና፣
➌ቆላ - ከባህር ጠለል በታች ጀምሮ እስከ 1500 ሜትር ከፍታ ያላቸው፣ የሙቀት መጠናቸውም ከ30 ዲግረ ሴ.ግ እስከ 50 ዲግረ ሴ.ግ የሚደርስ አከባቢዎች ናቸው።

ዋናው የዝናብ ወቅት ከሰኔ አጋማሽ እስከ መስከረም አጋማሽ ሲሆን፣ ከሱ ቀደም ብሎ አልፎ አልፎ የሚጥል የበልግ ዝናብ በየካቲት እና በመጋቢት ይከሰታል። የተቀሩት ወራት በአብዛኛው ደረቅ ናቸው።
•የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ነው

•አጠቃላይ ታሪክ

ከጥንት ጀምሮ ከነበሩ አገሮች የምትመደብና በአፍሪካ ከሚገኙ አገሮች ከሁሉም የበለጠ ረጅም እድሜ ያስቆጠረች አገር ነች፡፡ አምስት ሚሊዮን አመት የሚሆነውና በጣም ረጅም እድሜ ያስቆጠረው የሰው ቅሪት የተገኘው በኢትዮጵያ አዋሽ ሸለቆ አካባቢ ሲሆን ይህም፣ 3.2 ሚሊዮን አመት የሆነውን እዛው አካባቢ የተገኘውን የሉሲን /ድንቅነሽን/ አጽም በእድሜ ይበልጣል፡፡

በአራተኛው ክፍለ ዘመን ከግብጽና ሶሪያ ሚሲዮኖች መጥተው ክርስትናን ለኢትዮጵያ አስተዋውቀው ነበር፡፡ ነገር ግን በሰባተኛው ክፍለ ዘመን በእስልምና መስፋፋት ምክንያት ኢትዮጵያ ከአውሮፖውያኑ ክርስትና ርቃ ቆይታለች፡፡ ከዛም በ1500 ዎቹ ፖርቱጋሎች በህንድ ውቅያኖስ ላይ የነበራቸውን ይዞታ ለማጠናከርና ኢትዮጵያ ውስጥ የሮማ ካቶሊክን ለማስፋፋት ሲሉ ከኢትዮጵያ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት መልሰው ጀምረው ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት አንድ ክ/ዘመን ያህል የፈጀ የሀይማኖት ግጭት በ1630ዎቹ ተነስቶ ከውጪ የመጡትን ሚሲዮናዊያንን በሙሉ ከኢትዮጵያ ተባረው ሲወጡ ተፈጽሟል፡፡ ይህ የከፋ የግጭት ጊዜ ኢትዮጵያ የውጭ ክርስትያኖች ላይ እና አውሮፖውያኖች ላይ እስከ ሀያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ፊቷን እንድታዞር አስተዋጾ ከማድረጉም በተጨማሪ እስከ 19ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ ድረስ ኢትዮጵያ ከመላው አለም ተገልላ እንድትቆይ አድርጓታል፡፡

ከ1700ዎቹ ጀምሮ 100 ለሚሆኑ አመታት ኢትዮጵያ ማዕከላዊ አገዛዝ ሳይኖሯት ቆይታለች፡፡ ይህም "የመሳፍንት ዘመነ መንግስት" የተለያዩ የኢትዮጵያን ክፍል ይገዙ በነበሩ ገዢዎች መሀል በነበረው ፉክክር የተነሳ በመጣው ብጥብጥ ሲታወቅ በ1869 ግን አፄ ቴዎድሮስ መሳፍንቶችን አንድ ላይ በማምጣት ዋነኛ አሰባሳቢ ሀይል ሆነዋል፡፡ ተከታያቸው አፄ ዮሀንስም አፄ ቴዎድሮስ የጀመሩትን ቀጥለው ኢትዮጵያን ለመውረር ሙከራ ያደረጉትን ደርቡሾችና ሱዳኖችን ረተው መልሰዋል፡፡

ከ1881 እስከ 1905 ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ በአፍሪካ ይዞታቸውን እያሰፉ የነበሩትን የአውሮፖ ሀይሎችን ጥቃት በመከላከል ኢትዮጵያን ገዝተዋል፡፡ በዛ ጊዜ ጣልያን ኤርትራን በከፊል ቅኝ ገዝታ የነበረችበትና በ1880ዎቹ አጋማሽ ላይ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ቅኝ ገዝታት የነበረችበት ጊዜ ስለነበር ከሌሎች አውሮፖ አገራት በበለጠ ለኢትዮጵያ አስጊ ነበረች፡፡ በ1880 ግን እስከዛሬ ድረስ ዝነኛ በሆነው የአድዋ ጦርነት ኢትዮጵያ ጣልያንን አሸንፋ በአፍሪካ የቀኝ ገዥ ሀይሎችን ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች፡፡

በ1908 የክርስትና ሀይማኖት ሹማምንት ልጅ እያሱን ለእስላሙ ህብረተሰብ በመቆርቆራቸው ምክንያት ከስልጣን አውርደው የዳግማዊ ሚኒሊክ ልጅ የሆኑትን እቴጌ ዘውዲቱን ስልጣን ላይ አውጥተዋቸዋል፡፡ የሳቸው የቅርብ የስጋ ዘመድ የነበረውም ራስ ተፈሪ መኮንንም ሞግዚት አስተዳደርና ወራሽ ሆነው ተሹመዋል፡፡

እቴጌ ዘውዲቱ በ1922 ሲሞቱ ተተኪያቸው ስማቸውን ወደ ሀይለስላሴ በመቀየር ስልጣን ላይ ወጡ፡፡ ነገር ግን በ1928 ዓ.ም የጣልያን ሀይሎች ኢትዮጵያን ለአጭር ጊዜ ወረው ሲቆጣጠሩ ግዛታቸው ተቋርጦ ነበር፡፡ ይህን ጊዜም አፄ ሀይለስላሴ ለሊግ ኦፍ ኔሽንስ ይግባኝ ብለው ሰሚ ስላጡ ወደ እንግሊዝ ተሰደው ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የኢትዮጵያ አርበኞች ከብሪታንያ ጋር በመተባበር ጣልያንን እስኪያሸንፉ ድረስ ወደ ስልጣናቸው አልተመለሱም ነበር፡፡

አፄ ሀይለ ስላሴ እስከ 1966 ድረስ ስልጣን ላይ ከቆዩ በኋላ በምትካቸው የጊዜአዊ ወታደራዊ ምክር ቤት /ደርግ - ኮሚቴ የሚል ትርጉም ሲኖረው/ ስልጣን ይዘው በስም ሶሻሊስት የሆነ በአቋም ግን ወታደራዊ አመራር ያለው መንግስት ተመሰረተ። ከዚህ ክስተት በኋላ ሻለቃ መንግስቱ ሀይለ ማሪያም እንደ ኘሬዝዳንትና እንደ ደርግ ሊቀ መንበር ስልጣን ያዙ፡፡

በ1980ዎቹ መጀመሪያ በኢትዮጵያ በተለይ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በሚገኙት ትግራይና ኤርትራ መንግስታዊ ግልበጣ ተካሄደ፡፡ በ1981ዓ.ም የትግራይ ህዝቦች ነፃ አውጪ ግንባር /ትህነግ/ ከብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን/ እና ከኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ ጋር አንድ ላይ በመሆን የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ን መሰረቱ በግንቦት 1983 ላይም የኢህአዲግ ሀይሎች ወደ አዲስ አበባ በመግባት ኮሎኔል መንግስቱ ወደ ዙንባቢዌ እንዲሰደድ ሆኗል፡፡
በ1983 ከኢህአዲግ እና ሌሎች የአገሪቷ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተውጣጡ 87 የተወካዮች ምክር ቤትና በሽግግር ህገ መንግስት የኢትዮጵያ ሽግግር መንግስት ተቋቋመ፡፡
በዛው አመት በኢሳያስ አፈወርቂ መሪነት የኤርትራ ህዝቦች ነፃ አውጭ ግንባር /ኤህነግ/ ከ30 አመታት ትግል በኋላ ኤርትራን ተቆጣጥሮ ጊዜአዊ መንግስት መሰረተ፡፡ እስከ ግንቦት 1985 ዓ.ም ድረስም ኤርትራዊያኖች በተባበሩት መንግስታት ክትትል የጠየቁት የመገንጠል መብታቸውን እስኪያገኙ ድረስ የጊዜአዊው መንግስትም ስልጣን ላይ ቆየ፡፡
በኢትዮጵያም ኘሬዘዳንት መለስ ዜናዊና የሽግግር መንግስቱ አባላት በሰኔ በ1986 ዓ.ም 548 አባላት ባሉት ለህገ መንግስታዊ ምክር ቤቶች ምርጫ ተካሄደ፡፡ በ1987ዓ.ም መጀመሪያ ላይ የተመረጡት የምክር ቤቱ አባላት የኢፌዲሪን ህገ መንግስት ተቀበሉ፡፡ የፖርላማ ምርጫ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው በ1987 ዓ.ም ሲሆን በዛው አመት ነሀሴ ወር ላይ መንግስት ተቋቋመ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ

☞ይቀጥላል☜
3.5K views16:00
Open / Comment